Thursday, June 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ዘምዘም ባንክ ለሴቶችና ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን በማስተዋወቅ ቀዳሚ የሆነው ዘምዘም ባንክ፣ በአነስተኛ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ሴቶችና ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ልዩ ትኩረት ይሰጣል ያለውን ‹‹ዘምዘም ማኅበራዊ ፋይናንስ አገልግሎት›› መጀመሩን አስታወቀ።

ባንኩ ማክሰኞ መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. እንዳስታወቀው፣ አዲስ የተጀመረው አገልግሎት፣ ከሚሰጣቸው የማኅበራዊ ፋይናንስ አግልግሎቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በዚሁ አገልገግሎት ወጣቶች፣ ጎልማሶች፣ የአካል ጉዳተኞች፣ በአጠቃላይ ፆታ ሳይለይ በአነስተኛ የሥራ መስክ ላይ ለተሰማሩ የማኅበረሰበ ክፍሎች ለሥራ ማስጀመሪያ የሚሆን የፋይናንስ አቅርቦትና የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን በመስጠት ኢንተርፕርነሮቹ በተሰማሩበት የሥራ መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው፡፡

ዘምዘም ባንክ በአጠቃላይ የማኅበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሻሻል ከሚያደርገው ሁለንተናዊ ጥረት በተጨማሪ፣ ሴቶችን ማዕከል ያደረጉ የሴቶች ዋዲያህ የቁጠባ ሂሳብና ዘምዘም የሴቶች ሙዳራባህ የቁጠባና ኢንቨስትመንት የሒሳብ ዓይነቶችን በሥራ ላይ ማዋሉን፣ የአገልግሎቱን ተደራሽነት ለማስፋትና ምቹ ለማድረግ ‹‹ዘምዘም የሴቶች ኤሌክትሮኒክስ የግብይት ካርድን በአገሪቱ ባሉ በሁሉም ባንኮች የኤቲኤም ማሽኖች መጠቀም እንዲቻል ማድረጉንም ጠቁሟል፡፡ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅትም ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራውን ሀጀራ ቅርንጫፍ ማስተዋወቁንም አስታውሷል፡፡

ባንኩ ከጅምሩ የተዋቀረበት የባለ አክሲዮኖች ስብጥር፣ ሴቶች ተገቢውን ድርሻ የያዙ መሆናቸውን የሚያሳይ መሆኑንና ሴቶች በብቃታቸው ተወዳድረው ከዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ጀምሮ፣ ከዋና ሥራ አስፈጻሚ እስከ መካከለኛ የሥራ አመራር ኃላፊነት ቦታን በመያዝ ባንኩን እያገለገሉ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

 ባንኩ ትናንት ያስተዋወቀው ዘምዘም ማኅበራዊ ፋይናንሲንግ አገልግሎት መጀመርም፣ የሴቶችን ተሳትፎ ይበልጥ ለማጎልበትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየተጫወተ ያለውን ጉልህ ሚና የሚያረጋግጥ መሆኑን ማሳያ እንደሆነ አስረድቷል፡፡

በተጨማሪም ባንኩ የፋይናንስ አቅርቦቱን ሁሉን አካታች ከማድረግ ጎን ለጎን ደንበኞች ምቹና ዘመናዊ አሠራር ለመዘርጋት የዘምዘም የሞባይል አፕሊከሽንን በይፋ ማስጀመሩንና ደንበኞቹ የሞባይል አገልግሎቱን መተግበሪያ ከጉግል ፕሌይ ስቶር በቀላሉ በማውረድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጠቁሞ፣ ይህም የባንኩን ዘመናዊ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ወደላቀ ደረጃ የሚያሸጋግርና ተደራሽነቱንም የሚያሰፋ፣ ለደንበኞቹም ቀላልና ምቹ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን አብራርቷል።

የዘምዘም ማኅበራዊ ፋይናንሲንግ አገልግሎት መጀመርም የሴቶችን ተሳትፎ ይበልጥ ለማጎልበትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑን አስረድቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች