የሥነ አካባቢ ሳይንቲስቱ ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር (ዶ/ር)፣
ግለ ታሪካቸውን የምድራችን ጀግና በሚል ርዕስ ላዘጋጀው ዘነበ ወላ የነገሩት፡፡ ማንንም ሰው በእኔ ሕይወት ውስጥ እምነቱን አከብርለታለሁ። እኔም እንዲሁ አመለካከቴን እንዲያከብሩልኝ እፈልጋለሁ። በዚህም አመለካከት ዓለምን አገሬ አድርጌያለሁ ያሉት ነፍስ ኄር ተወልደ ብርሃን፣ ሰው ሁሉ ሰው ነው። ሰው ሁሉ የትም ይፈጠር እኩል ነው የሚለውን እምነት በተጨባጭ እያሳዩ ያሳደጓቸው ወላጆቻቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።