Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየስታዲየም ዕገዳ ከተጣለባቸው አራት የአፍሪካ አገሮች ኢትዮጵያ ብቻ ግንባታዋን አለማጠናቀቋን ፌዴሬሽኑ አስታወቀ

የስታዲየም ዕገዳ ከተጣለባቸው አራት የአፍሪካ አገሮች ኢትዮጵያ ብቻ ግንባታዋን አለማጠናቀቋን ፌዴሬሽኑ አስታወቀ

ቀን:

  • ሞሮኮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወጪን 73 ሺሕ ዶላር ይሸፍናል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የካፍ ደረጃን አላሟሉም ተብለው ዕግድ ከተጣለባቸው አራት የአፍሪካ አገሮች ኢትዮጵያ ብቻ የስታዲየም ግንባታዋን አለማጠናቀቋን ገለጸ፡፡

አኅጉራዊው የእግር ኳስ መሪው ካፍ የጊኒ፣ የሞዛምቢክና የሩዋንዳ አገር ስታዲየሞች የካፍ ደረጃን አያሟሉም ብሎ ያገዳቸው ሲሆን፣ አገሮቹ ግንባታቸውን አጠናቀው የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን አስታውቀዋል፡፡

የዋሊያዎቹ በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን በተመለከተ፣ መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓ.ም. መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ በኢትዮጵያ እየተገነቡ የሚገኙት ስታዲየሞች ባለመጠናቀቃቸው ፌዴሬሽኑ ለእንግልት ተዳርጓል ተብሏል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ የካፍን መሥፈርት ማሟላት የሚችል ስታዲየም ማጣቷ ዋጋ እያስከፈለን ነው፤›› በማለት የሚያስረዱት አቶ ባህሩ፣ የፊፋን ጉባዔ ያዘጋጀችው ሩዋንዳ እንደ ኢትዮጵያ የታገደች ብትሆንም፣ ሰው ሠራሽ ሳር ያለበት ስታዲየም ገንብታ ማስመረቋን ያነሳሉ፡፡

ሌላዋ የአፍሪካዊት አገር ጊኒ በካፍ ከታገዱ አገሮች መካከል አንዷ ብትሆንም፣ በቅርቡ እያስገነባችው የምትገኘው ስታዲየም የመጨረሻ ምዕራፍ ደርሶ፣ የካፍ ግምገማ ቡድን ስታዲየሙ ያለበትን ደረጃ መመልከቱን አቶ ባህሩ አንስተዋል፡፡

‹‹ከኢትዮጵያ ጋር ቅጣት የተላለፈባቸው የሩዋንዳ፣ ጊኒና ሞዛምቢክ የስታዲየሞችን ግንባታ ማጋመስ ችለዋል፡፡ በአንፃሩ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለች ትገኛለች፤›› በማለት አቶ ባህሩ ተናግረዋል፡፡

እንደ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ማብራሪያ መሠረት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታዎችን በሜዳው ባለማድረጉ በሜዳው ሊያገኘው የሚችለውን የተመልካች ድጋፍ በማጣቱ ተጎድቷል፡፡ ከዚያም ባሻገር የብሔራዊ ቡድኑ የሌሎች አገሮች ስታዲምን በመጠቀሙ ለከፍተኛ ወጪ መጋለጡና ብሔራዊ ፌዴሬሽኑንም ለኪሳራ ዳርጎታል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያና የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች የጋራ ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ፣ ብሔራዊ ቡድኑ በሞሮኮ የሚያደርገውን የቆይታና የተለያዩ ወጪዎች በሞሮኮ እግር ኳስ ፈዴሬሽን እንደሚሸፈን አቶ ባህሩ አስረድተዋል፡፡

የብሔራዊ ቡድኑ የሆቴል ወጪ፣ የልምምድ ቁሳቁስ ወጪዎች፣ እንዲሁም ከስታዲየም ጋር የተያያዙ ወጪዎች ሞሮኮ እንደሚሸፈን ተገልጿል፡፡ በአጠቃላይ የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለሚያደርገው ዝግጅት 73 ሺሕ ዶላር ወጪ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ አራተኛ የምድብ ጨዋታውን የሚያስተናግድበትን ስታዲየም ለይቶ እንዲያሳውቅ ካፍ ፌዴሬሽኑን መጠየቁን የፌዴሬሽኑ የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አስታውሰዋል፡፡

በዚህም መሠረት በአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) ማጣሪያ ጨዋታ ወቅት ብሔራዊ ቡድኑ ታንዛኒያ ላይ ጨዋታውን ማድረጉን ተከትሎ፣ የመጀመርያ ምርጫውን ታንዛንያ እንደነበር በጋዜጣዊ መግለጫው ጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሚመርጠውን ስታዲየም ለተጋጣሚ ካሳወቀ በኋላ፣ ከጊኒ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመመካከር የምድቡን ጨዋታ በሞሮኮ ለማድረግ ከውሳኔ መድረሱን አቶ ባህሩ አስረድተዋል፡፡

በስታዲየም ምርጫ ሒደት ከአሠልጣኞች ጋር ውይይት መደረጉን የጠቀሱት አቶ ባህሩ፣ በሞሮኮ ያለውን የአየር ንብረት ሁኔታ በማጤን እንደተወሰነ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የስፖንሰርሸፕ አማራጮችን ሲያፈላልጉ መቆየቱን አብራርተው፣ ብሔራዊ ቡድኑ የማጣሪያ ጨዋታውን ሲያከናውን ከ1xbet የስፖርት ውድድር ድርጅት ጋር የሜዳ ላይ የማስታወቂያ ቦርድ (Pitch Branding) ለማስቀመጥ የ8,000 ዶላር የስፖንሰርሽፕ ስምምነት መፈራረሙን አስታውቋል፡፡

በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚከናወን የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎችን በማድረግ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጊኒ አቻውን ለመግጠም ወደ ሞሮኮ አቅንቷል፡፡

ዋሊያዎቹ የምድብ ጨዋታቸውን መጋቢት 15 ሲያደርጉ፣ ቀጣዩን መጋቢት 18 ቀን እንደሚያደርጉ ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...