Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፓርላማው በሕወሓት የሽብርተኝነት ስያሜ ላይ ዛሬ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል

ፓርላማው በሕወሓት የሽብርተኝነት ስያሜ ላይ ዛሬ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል

ቀን:

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የሰየመውን ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የሽብርተኝነት ስያሜ ይነሳ አይነሳ በሚለው ጉዳይ ላይ ዛሬ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በምክር ቤቱ ውስጥ የብልፅና አባላት ሕወሓትን ከአሸባሪነት ለመሰረዝ ያለመ ዝግ ስብሰባ ትናንት መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔን ጨምሮ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን በተገኙበት ሲያካሂድ እንደዋለና በውይይቱም በርካታ መግባባት ያላስቻሉ ጠንካራ ሐሳቦች መሰንዘራቸውን ሪፖርተር ከምንጮቹ ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ይሁን እንጂ በፓርላማው የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን የ2014 በጀት ዓመት የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት ላይ ለመምከር ለመጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ለጠዋት ጠርቶት የነበረውን ስብሰባ ወደ ከሰዓት በማጠፍ፣ በዚሁ ቀን ጠዋት አስቸኳይ ስብሰባ ለፓርላማ አባለቱ መላኩ ተገልጿል፡፡

ፓርላማው ሕወሓትንና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ድርጅት ወይም በመንግሥት ‹‹ሸኔ›› ተብሎ የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን በአሸባሪነት የፈረጀው በሚያዚያ በ2013 ዓ.ም. ነበር፡፡

የፌዴራል መንግሥቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት ያህል በአሸባሪነት ከተሰየመው ሕወሓት ታጣቂዎች ጋር ጦርነት ሲያካሂድ ከቆየ በኋላ፣ ከጥቂት ወራት በፊት መንግሥት ከዚሁ በአሸባሪነት ከተሰየመው ድርጅት ጋር ከሽብርተኛ አባልነቱ በፓርላማው ሳይሰረዝ፣ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ያካሄደ ሲሆን፣ ሐወሓትም ከሌሎች አካላት ጋር በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለመመሥረት ወደ ሥራ መግባቱ ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...