Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽሕፈት ቤትና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ አረፉ

የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽሕፈት ቤትና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ አረፉ

ቀን:

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤትና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) አረፉ፡፡

 ልዩ ጽሕፈት ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው፣ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ያረፉት ትናንት መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ነው፡፡

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም.  ከተሾሙት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ የነበሩት፣ በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለማርያም መለሰ (ዶ/ር)፣ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ለረጅም ጊዜ ከአገር ውጪና በአገር ውስጥ በሕክምና ሲረዱ ቆይተዋል፡፡

በቤተክርስቲያን ትምህርት ቅኔን ከግጨው መንክር ምንዝሮ ተክለ ሃይማኖት፣ ሐዲሳትን ከመጋቤ ሐዲስ ወልደ ሰንበት ግምጃ ቤት ማርያም የተማሩት ብፁዕነታቸው፣ የመጀመርያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአፄ ፋሲልና በዳግማይ ደብረ ሊባኖስ አዘዞ ሃይማኖት ትምህርት ቤቶች ተምረዋል። ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ትምህርት ቤትም  በቲኦሎጂ ዲፕሎማ፣ እንዲሁም ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በቲኦሎጂ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡

ለከፍተኛ ትምህርት ባህር ማዶ በመሻገር ከኖርዌይ ስታሻንገር ስፔሻሊይዝድ ዪኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ፣ ከፕሪቶርያ ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና የፒኤችዲ ዲግሪ ማጠናቀቃቸው በዜና ሕይወታቸው ተመልክቷል፡፡

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የቦርድ አባል፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የቦርድ አባል በመሆን፣ የቅድስት ልደታ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የቦርድ አባል በመሆንም ሠርተዋል። በዓለም አቀፍ ተሳትፎ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕድ ቤተ ክርስቲያንን በመወከል የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣ የመላው ኦሪየንታል ኦርቶዶስ አብያተ ክርስቲያናትን በመወከል የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ሠርተዋል።

የብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ሥርዓተ ቀብር በሳምንቱ መገባደጃ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...