Thursday, March 23, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የኦፓልና ሳፋየር ማዕድናት ግብይትን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት መጀመሩን አስታወቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • አኃዱ ባንክ ጋር በጋራ ለመሥራት ተፈራረመ

ከግብርና ምርቶች በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ምርቶችን፣ እንዲሁም ኦፓል፣ ሳፋየርና ኢመራልድ የማዕድን ምርቶችን ወደ ግብይት ሥርዓት ለማስገባት ቅድመ ዝግጅት መጀመሩን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የማዕድን ግብይት ለመጀመር በሒደት ላይ መሆኑን የተናገረው፣ መጋቢት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ከአኃዱ ባንክ ጋር አብሮ ለመሥራትና አሠራሩንም ለማዘመን 21ኛ የክፍያ አጋሩ አድርጎ ለመሥራት ስምምነት በተፈራረሙበት ዕለት ነው፡፡

በስምምነቱ መሠረት፣ ተገበያዮች ግብይቱን በፈጸሙ ማግሥት ለአቅራቢዎች የሸጡበትን ገንዘብ በቀጥታ ከገዥው የባንክ ሒሳብ ወደ ሒሳባቸው ለማዞር የሚከናወነውን ሥራ ከማሳደግም በላይ፣ የክፍያ ሥርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚረዳ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ እንደገለጹት፣ በአስተማማኝ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ዘመናዊ የክፍያና የርክክብ ሥርዓትን በመታገዝ ሻጮች ምርታቸውን በሸጡ ማግሥት ገንዘባቸውን ወደ ባንክ ሒሳባቸው በማስገባት ላለፉት 15 ዓመታት ያለ ምንም መጓደል አገልግሎት በመስጠት የበኩሉን ተወጥቷል፡፡

ምርት ገበያው በኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ 22 ምርቶችን ወደ ግብይት ሥርዓቱ በማስገባት ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡ ‹‹ተቋሙም ከግብርና ምርቶች በተጨማሪ ከኢንዱስትሪ ምርቶች፣ ስኳር፣ ሲሚንቶና የኢንዱስትሪ ጨው፣ ከማዕድን ምርቶች ኦፓል፣ ሳፋየርና ኢመራልድን ወደ ግብይት ሥርዓት ለማስገባት ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም በውል ላይ የተመሠረተ ወደፊት የሚፈጸም ግብይት (Customized Forward Trade) የልኅቀት ማዕከል በሚሆነው የምርት ገበያው አካዴሚ፣ ተጨማሪ የመጋዘን የጥራት ፍተሻ አገልግሎት ለመስጠት ዕቅድ መያዙንም አቶ ወንድማገኘሁ ተናግረዋል፡፡

ወደ ግብይት ሥርዓቱ የሚገቡ አቅራቢዎች፣ ኅብረት ሥራ ማኅበራትና ላኪዎች፣ የዚህ የክፍያ ሥርዓት ተገልጋይና ተጠቃሚ ስለሚሆኑ ለጤናማ ግብይት፣ እንዲሁም ለአስተማማኝ ሕጋዊ የገንዘብ ፍሰት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል፡፡

ባለፉት 15 ዓመታት ወደ ምርት ገበያው የመግዣ አካውንቶች ከገዥው ለግብይት የገባውና ለሻጮችም በምርት ገበያው አማካይነት የተከፈለው የገንዘብ መጠን ከ3.68 ቢሊዮን ብር ባላይ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

በተለይ እነዚህን ሁሉ ግብይቶችና አገልግሎቶች ሕጋዊ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ ስለሚያልፉ፣ ከምርት ገበያው ጋር የሚሠሩ ባንኮችን የደንበኞቻቸውን ቁጥር እንዲያሳድጉና የአገልግሎት አድማሳቸውን እንዲያሰፉ ያደርጋቸዋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጋር የተደረገው ስምምነት በዋነኛነት የምርት ገበያው በሚያገበያያቸው ምርቶች ንግድ ላይ የተሰማሩ ደንበኞችን በሚገባ ለማገልገል የሚያስችል ነው ያሉት የአኃዱ ባንክ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰፊዓለም ሊበን ናቸው፡፡     

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች