Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየሳዑዲ ዓረቢያና የኢራን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዳግም መመለስ

የሳዑዲ ዓረቢያና የኢራን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዳግም መመለስ

ቀን:

ሳዑዲ ዓረቢያና ኢራን በየግላቸው በቀጣናው ላይ መፍጠር በሚፈልጉት ተፅዕኖና በእስልምና አስተምህሯቸው ምክንያት ለበርካታ ዓመታት በውጥረት ውስጥ ከርመዋል፡፡ ይህም ሳዑዲ ዓረቢያ ከአሜሪካ፣ ኢራን ደግሞ ከሩሲያ ጋር እንዲወግኑ አድርጎ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

አሜሪካና ሩሲያ የውክልና ጦርነት ባደረጉባቸው ሶሪያና የመንም ሁለቱ አገሮች በተዘዋዋሪ መሳተፋቸው አልቀረም፡፡ በውስጥ የፖለቲካ ጉዳያቸውም ቢሆን አንዱ ለአንዱ ጠላት እንጂ ወዳጅ አልነበሩም፡፡ ይህም በየአገሮቹ መሀል ውጥረት አንግሶ ከርሟል፡፡

ይህ የሻከረው የአገሮቹ ግንኙነት ወደ ቀድሞ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ ይመለስ ዘንድ፣ የአሁኑ የኢራን ፕሬዚዳንት ሰይድ ኢብራሂም የወሰዱት ዕርምጃ ዛሬ ላይ ፍሬ አፍርቷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እ.ኤ.አ. በነሐሴ 2021 የኢራን ስምንተኛ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ፕሬዚዳንት ኢብራሂም፣ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ለመሥራት ቃል ከገቡባቸው ጉዳዮች አንዱ ኢራን ከጎረቤት አገሮች ጋር ያላትን ግንኙነት ማሻሻልና ማጠናከር ነበር፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው፣ በቻይና አደራዳሪነት ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ የመጡት ኢራንና ሳዑዲ ዓረቢያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ዳግም ለማስቀጠል ተስማምተዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በቻይና ቤጂንግ የተወያዩት የኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ሴክሬታሪ ዓሊ ሻምካኒና የሳዑዲ ዓረቢያ ብሔራዊ የደኅንነት አማካሪ ሙሳድ ቢን ሞሐመድ፣ በቀጣይ ሁለት ወራት ውስጥ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን አጠናከረው ኤምባሲዎቻቸውን ለመክፈት ተስማምተዋል፡፡

ስምምነቱን ተግባራዊ ካደረጉ በኋላ የሁለቱ አገሮች አምባሳደሮችን መሾምን በተመለከተ የየአገሮቹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚመክሩ ይሆናል፡፡

ቻይና ሙሉ ድጋፏን የሰጠችበት የአገሮቹ ስምምነት በየአገሮቹ አምባሳደር ከመሾምና ኤምባሲዎች ከመክፈት በተጨማሪ፣ የየአገሮቹን ሉዓላዊነት ለማክበርና በውስጥ ጉዳያቸው ጣልቃ ላለመግባት ተስማምተዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2001 የተስማሙበትን የደኅንነት ትብብር ዳግም ለማስጀመር የተስማሙ ሲሆን፣ ይህ ከ22 ዓመታት በፊት ያስቀመጡት ስምምነት በጋራ ሆነው ሽብርተኝነትን መዋጋት፣ የአደንዣዝ ዕፅና ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን መዋጋት፣ እንዲሁም በንግድና በቴክኖሎጂ ዙሪያ አብሮ መሥራትን ያካተተ ነው፡፡

በሁለቱ አገሮች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት ማስወገድና የወደፊት ሁነቶች ላይ ያተኮረ ግንኙነት በመፍጠር በቀጣናው መረጋጋትና ደኅንነትን ማረጋገጥ የስምምነቱ አካል ነው፡፡

በኢራንና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የተደረሰው ዲፕሎማሲያዊ ስምምነትም የፐርሺያ ባህረ ሰላጤ አገሮችንና የሙስሊሙን ዓለም እያጋጠሟቸው ያሉትን ፈተናዎች ለመወጣት ያስችላቸዋል ሲሉ ሴክሬታሪው ዓሊ ሻምካኒ ተናግረዋል፡፡

ሳዑዲ ዓረቢያ ከኢራን ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እ.ኤ.አ. በ2016 ማቋረጧ ይታወሳል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ሳዑዲ ዓረቢያ ታዋቂ የሙስሊም ምሁር በሞት መቅጣቷን ተከትሎ በኢራን የሚገኙ የሳዑዲ የዲፕሎማቲክ ቢሮዎች በኢራን ተቃዋሚዎች መወረራቸው ነበር፡፡

ከዚህም አስቀድሞ በሁለቱ አገሮች የነበሩ መካረሮች ግንኙነቶችን ከማሻከራቸው ባለፈ፣ በየመን ያለውን ጦርነት ጎራ ለይተው እንዲያፋፍሙ፣ በሊባኖስና በሶሪያ ጉዳይ በመግባትም ችግሮችን እንዲያባብሱ አድርጓል፡፡

በሁለቱ አገሮች መካከል የነበረው መካረር በአጠቃላይ በቀጣናው ውስጥ ለሚከሰቱ አለመረጋጋቶች ትልቁን ድርሻም ይዞ ነበር፡፡

የአልጀዚራው ተንታኝ ዓሊ ሐሺም እንደሚለው፣ በሁለቱ አገሮች መካከል የተደረሰው ስምምነት በመካከለኛው ምሥራቅ ፖለቲካ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡

በየመን፣ በሶሪያና በሊባኖስ ያሉ አለመግባባቶች ዕልባት እንዲያገኙም ዕድል ይፈጥራል፡፡ በቀጣናው የተሻለ መረጋጋትና ሰላም እንዲሰፍንም ያስችላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...