Monday, June 24, 2024
Homeስፖንሰር የተደረጉአየርላንድ እና ኢትዮጵያ፡ ታሪካዊ አጋርነት

አየርላንድ እና ኢትዮጵያ፡ ታሪካዊ አጋርነት

Published on

- Advertisment -

ከሁሉም በዓላት የላቀ የሆነውና የአየርላንድ ብሔራዊ በዓል በመሆን የሚታወቀው የቅዱስ ፓትሪክ ቀን በመላው ዓለም በሰልፍ፣ በመዝናኛ ፓርቲዎች እና በደማቅ ሁኔታ፣ እንዲሁም ደግሞ የአየርላንድን ባሕል፣ ሙዚቃ እና ዳንስ ትርዒቶች አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ ይከበራል። ዕለቱም አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የረዥም ጊዜ ግንኙነት መለስ ብለን የምናሰላስልበት ጊዜ ነው፣ ይህም ደግሞ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ኢሞን ደ ቫሌራ በመንግስታቱ ማህበር (በሊግ ኦፍ ኔሽን) የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በጥብቅ የሚደግፍ መግለጫ ከሰጡበት ከ 1936 ዓ.ም. አንስቶ የሚጀምር ነው።  በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይቅዱስ ቁርባን ስርአትን ከሚያሳየው ስዕል አጠገብና በአስደማሚው ሃይማኖታዊ ሥዕላዊ መግለጫ ውስጥ፣ የመንግሥታቱን ማህበር ጉባኤ የሚያሳይ ስዕል አለ። የምስሉ ትኩረት የአፄ ኃይለ ሥላሴ የአገራቸውን ወረራ በመቃወም የእርዳታ ጥሪ ያቀረቡበት አቤቱታ ላይ ነው። ከዚህ በስተጀርባም ለንጉሰ ነገስቱ አቤቱታ ጠንካራ ድጋፋቸውን ለማሰማት በዝግጅት ላይ የነበሩት የወቅቱ የአየርላንድ ጠቅላይ ሚ/ር ዴ ቫሌራ ይታያሉ።

ይኽን ታሪካዊ አሻራ ይበልጥ በሚገነባ መልኩም፣ አየርላንዳዊው ዘፋኝ ቦብ ጌልዶፍ የገና በዓል መሆኑን ያውቃሉ? በሚለው ነጠላ ዜማውና እና በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 1977 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1985 ዓ.ም) ባዘጋጀውና በዓለም አቀፍ ደረጃም በቀጥታ በተላለፉ የሙዚቃ ኮንሰርቶች አማካኝነት እርዳታ ኮንሰርቶች ለኢትዮጵያ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ፓውንድ ለኢትዮጵያ የረሃብ ተጎጂዎች ለማሰባሰብ ችሏል። የጌልዶፍ የማሳመን ብቃትም ኢትዮጵያን እና ገጥመዋት የነበሩ ተግዳሮቶችን በአየርላንድ እና በመላው ዓለም ሁሉ ይበልጥ እንዲታወቁ አግዟል።

በ 1986 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. በ 1994) የአየርላንድ ኤምባሲ በአዲስ አበባ መከፈቱ የአገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነትና ለረዥም ጊዜያትም ቅድምያ በተሰጣቸው እንደ ጤና፣ የተቀናጀ የአየር ንብረትና የምግብ ዋስትና፣ እንዲሁም ማህበራዊ ጥበቃ ባሉ ጉዳዮች ላይ መሰረት ያደረገ የልማት ትብብር እንዲፋጠን አድርጓል። ከኤምባሲው መከፈት በኋላ በመጡት ቀጣዮች ዓመታት ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት እየዳበረ ሄዶ አሁን ላይ ሰፊ የዲፕሎማሲ፣ የልማት ትብብር፣ የባህል እና የንግድ ግንኙነቶችን የሚሸፍን ሲሆን ዋነኛ የትኩረት ነጥቦቹም የጾታ እኩልነት እና ሰብአዊ ተግባራት ሆነዋል።

የአየርላንድ የቀድሞ ፕሬዝደንት ሜሪ ሮቢንሰን በ 2008 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. በ 2016) በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው በነበረበት ወቅት፣ የአየር ንብረት ለውጥ በጣም ተጋላጭ በሆኑ ህዝቦች ላይ ከባድ ተጽእኖ ማድረሱን በመቀጠሉ የካርቦን ልቀትን በመቀነስ ረገድ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪ አድርገው ነበር። ፕሬዝደንት ሮቢንሰን በንግግራቸው በአጽንኦት ሲናገሩም “የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎች የልማት ግኝቶችን ማዳከማቸውን እና የሰዎችን ለተፈጥሮ አደጋዎች ተጋላጭነታቸውን እየጨመሩ በመቀጠላቸው ምክንያት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የካርቦን ልቀትን የመቀነስ፣ ክፉኛ የተጎዱ ማህበረሰቦች ውስጥ የሚከናወኑ አደጋን የመቋቋም እና የማላመድ ጥረቶችን የመደገፍ ግዴታ አለበት” ብለዋል።

የአየርላንድ ጠቅላይ ሚ/ር ሊዮ ቫራድካር በ 2011 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. በ 2019) በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ከፕሬዝዳንቱ ጋርም ያደረጉት ውይይት በአየርላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የፖለቲካ ግንኙነት ጥልቅ እየሆነ መሄዱን ያመላከተ ነበር። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የአየርላንድ ጉብኝትም ልምድ የመለዋወጥ ፍላጎትን እና የመንግስት ለመንግስት እንዲሁም የንግድ ግንኙነቶችን በማሳደግ ረገድ ያለውን ፍላጎት አጉልቶ አሳይቷል። የቅዱስ ፓትሪክ ቀን የሚያጋምዱን ብዙ ነገሮች እንዳሉን፣ ለአገራችን ያለንን ፍቅር፣ ለአካባቢያችን የምናደርገውን ጥበቃ፣ የህዝቦቻችንን ልማት እና ግንኙነታችንን የማደስ እና ለመጪው ብሩህ ጊዜም በጋራ የመስራትን አስፈላጊነት ያስታውሰናል።

ይህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ የአየርላንድ ኢምባሲ ተዘጋጅቶ የቀረበ ለገፁ ክፍያ የተከፈለበት ነው፡፡

የቅርብ ጊዜ መጣጥፎች

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና ሆኗል፡፡ ሰዎች የተለያዩ ወጪዎቻቸውን ሸፍነው...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ ባለፀጋ ልጆች የሆኑ ሁለት ሰዎች...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ የተጠቀሱት ዓለማዊና አካባቢያዊ የተሞክሮ ትምህርቶች፣...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን አገልግሎት ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡ የሚከፍሉትን የገንዘብ...

ተመሳሳይ

ወንድማማቾቹን ለከፍተኛ ጉዳት የዳረገው ብሔር ተኮር ግጭት

ኢትዮጵያን በርካቶች የብዙኃን እናት፣ የብዙኃን አገር፣ ሲሉ ይጠሯታል፡፡ ለዚህም የተለያዩ ማንነቶች፣ ባህሎችና ሃይማኖቶች መኖሪያ...

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም በቶነር አሴምብሊንግ ስራ የተሰማራ ድርጅት...

ኦርቶፔዲክስ

በጡንቻ መገጣጠሚያ እና የአጥንት ህመሞች ላይ የላቀ ጥበብ፡- የአጥንት ጉዳትን ችግር ከመመርመርም ያለፈ የአጥንትና መገጣጠሚያ...