Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለሕንፃ ግንባታ ተቆፍሮ በተተወ ጉድጓድ ውስጥ የሰው ሕይወት አለፈ

ለሕንፃ ግንባታ ተቆፍሮ በተተወ ጉድጓድ ውስጥ የሰው ሕይወት አለፈ

ቀን:

ዓርብ መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን እየገነባው ባለው ማሪዮት ሆቴል ሕንፃና በጂቡቲ ኤምባሲ መሀል ለሕንፃ መሥሪያ ተቆፍሮ በተተወ በውኃ የተሞላ ጉድጓድ ውስጥ፣ አንድ ወጣት ለመዋኘት ገብቶ ሕይወቱ አለፈ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የድንገተኛ ቡድን መሪ ወ/ሮ ትዕግሥት ተክለአብ፣ ‹‹አደጋው የደረሰው ምሳ ሰዓት አካባቢ ሲሆን፣ ሁለት ጓደኛሞች ከምሳ በኋላ እንዋኝ ብለው ገብተው አንዱ ሰምጦ ሲቀር፣ በሕይወት ተርፎ በወጣው ጥቆማ መሠረት አደጋው መከሰቱን ለማወቅ ተችሏል፤›› ብለዋል፡፡

ሟች በግምት ከ27 እስከ 30 ዓመት ሊሆነው አንደሚችልና በአካባቢው በቀን ሥራ ላይ ተሰማርቶ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ጉድጓዱ እስከ ሦስት ሜትር የሚደርስ ጥልቀት እንዳለው፣ በውስጡም ተጀምሮ የቆሙ የብረት ምሰሶዎችና ቁርጥራጭ እንጨቶች በመኖራቸው፣ የአስከሬኑን ፍለጋ ከአንድ ሰዓት በላይ እንዲፈጅ እንዳደረገው፣ ኃላፊዋ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ቦታው ቀድሞ ለባለሀብት ተሰጥቶ የነበረ መሆኑንና አሁን ግን ከባለሀብቱ ተነጥቆ በመንግሥት ሥር እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ቦታው በአሁኑ ጊዜ አጥሮቹ ከመፈራረሳቸውም በላይ፣ ጉድጓዱም በተጠራቀመው ውኃ አረንጓዴ ለብሶ ሐይቅ መስሎ ይታያል፡፡ ይህን መሰል ጉድጓዶች በአካባቢው በብዛት ሲኖሩ፣ የቆሻሻ መጣያና የመፀዳጃ ቦታ በመሆናቸው አደጋ የመፍጠር አቅማቸው ከፍተኛ እንደሆነ ወ/ሮ ትዕግሥት አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...