ታገሱኝ ኃያላን በጋውን፥
እንዲሁም መጸውን፥
እስክጽፈው ግጥሜን፡፡
ያኔ ልቤ እያዜመ በታላቅ ደስታ፥
ፈቃዱ ይሆናል ለዘለዓለማዊ እንቅልፍ ለመኝታ፡፡
ግልጽ ነው አውቃለሁ የአርባ ቀን ዕድሏን ያልተቀበለች ነፍስ፥
ልትመኝ ቀርቶባት ገነትን ለመውረስ፥
ከወዲያኛው ዓለም አትችልም ለመድረስ፡፡
ግን ጊዜን ተችሮኝ ያንን ቅዱስ ተግባር ከቻልኩ ለመፈጸም፥
ከልቤ አመንጭቼ ከገጠምኩኝ ግጥም፥
ከወቀሳም ድኜ አገኛለሁ ሰላም፡፡
ያለማወላወል እቀበለዋለሁ በጸጋ ሞትንም፡፡
እንደ አማልክት ሁሉም ሰማይ እኖራለሁ፡፡
ከዚያ ወዲያ ተድላ ምን እፈልጋለሁ፡፡
- ተርጓሚዎች እነ ዘሪሁን አስፋው ‹‹የጀርመን ቅኔያት ከወልፍጋንግ ገተ እስከ ጉንተር ግራስ›› (1993 ዓ.ም.)