Wednesday, June 19, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ ተቋቋመ ስለተባለው የሽግግር መንግሥት ከአማካሪያቸው መረጃ እየጠየቁ ነው]

 • እኛ ሳንፈቅድ እንዴት ሊያቋቁሙ ቻሉ? ስምምነታችን እንደዚያ ነው እንዴ?
 • በስምምነታችን መሠረትማ እኛ ሳንፈቅድ መቋቋም አይችልም። የእኛ ተወካዮችም በአባልነት መካተት አለባቸው።
 • ታዲያ ምን እያደረገ ነው? ስምምነቱን መጣሳቸው ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር እነሱ እንደዚያ አላደርግንም፣ የፌዴራል መንግሥት ሳያጸድቀው የሽግግር መንግሥት አይመሠረትም እያሉ ነው።
 • ታዲያ ምንድነው የሠሩት?
 • ረቂቁን ነው የሠሩት።
 • ረቂቅ ምን?
 • ረቂቅ መንግሥት።

[ክቡር ሚኒስትሩ ከባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው የከተማ አስተዳደሩን ኃላፊ እየገመገሙ ነው]

 • ባለፈው በተገናኘንበት ወቅት የተለያዩ ማሳሰቢያዎችን ሰጥቼ ነበር።
 • አዎ። ትክልል ነው ክቡር ሚኒስትር
 • ለምሳሌ በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች በ90 ቀን መፈጸም የሚችሉ ፕሮጀክቶች ተለይተው እንዲተገበሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቼ ነበር።
 • አዎ።
 • እኮ ከምን ደረሰ?
 • በሁሉም የከተማው ክፍሎች ተጀምሯል። በተለይ በአዲሱ ክፍለ ከተማ አመቺ ቦታ በመኖሩ የተለያዩ የ90 ቀን ፕሮጀክቶችን እየተገበርን እንገኛለን።
 • ለምሳሌ ምን ተተገበረ?
 • የጓሮ አትክልቶችና መመገቢያ ማዕከላትን አጠናቀናል በተጨማሪም የከብት ዕርባታ ፕሮጀክት…
 • ከብት ዕርባታ በ90 ቀን?
 • ከብቶቹ በ90 ቀን እንደማይደርሱ የተረዳነው ፕሮጀክቱን ከጀመርን በኋላ ነው።
 • ስለዚህ ፕሮጀክቱ ታጠፈ?
 • አልታጠፈም። መፍትሔ አበጅተንለታል።
 • ምን አደረጋችሁ?
 • የደረሱ ከብቶችን ለይተን አስገብተናል።
 • ለምን የደረሱ?
 • ለመታለብ።
 • ማሳሰቢያ የሰጠሁት ግን ለአንድ ክፍለ ከተማ ብቻ አይደለም።
 • ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • አመራሩ ቢሮ መዋልና በቪኤይት መንፈላሰስ ከዚህ በኋላ አይችልም። ፒክአፕ እየነዳ ፕሮጀክቶችን ይከታተል ብዬ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቼ እንዴት እስካሁን አይጀመርም?
 • በማሳሰቢያው መሠረት የከተማ አመራሩ ቪኤይት እንዳይነዳ ከልክለን ጎን ለጎን የጀመርነውን ጨረታ ሰሞኑን አጠናቀናል።
 • የምን ጨረታ?
 • የፒክ አፕ።
 • ምን?
 • አመራሩ ፒክ አፕ እየነዳ ፕሮጀክቶችን እንዲከታተል በሰጡት ማሳሰቢያ መሠረት የተፈጸመ ነው።
 • አመራርነት በቪኤይት መንፈላሰስ አይደለም ብል ፒክ አፕ ገዛችሁ?
 • በግልጽ እኮ ነው የገዛነው?
 • በግልጽ ማለት?
 • በግልጽ ጨረታ።
 • እሺ ሌላስ ምን ገዛችሁ?
 • አመራሩ ፒክ አፕ ቢመደብለትም ቢሮ መዋሉን ሊተው ባለመቻሉ ይህንን የሚያስቀር ግዥ እንዲፈጸም ወስነናል።
 • የምን ግዥ?
 • ለእያንዳንዱ አመራር በደረጃው ልክ ዘመናዊ ላፕቶፕና ሞባይል ስልክ እንዲገዛ።
 • ምን?
 • አዎ። ከዚህ በኋላ ቢሮ ለመዋል ምክንያት አይኖራቸውም። ባሉበት ሆነው በስልካቸው ወይም በላፕቶፕ መገልገል ይችላሉ።
 • እኔ ያልኩት ሕዝብ እንድታገለግሉና ቢያንስ የአቅመ ደካሞችን ቤት እንድታድሱ፣ እንድትጠግኑ እንጂ …
 • ክቡር ሚኒስትር ስለእሱም ተወያይተን ወስኔ አሳልፈናል።
 • ምን?
 • አመራሩ የአቅመ ደካሞችን ቤት ለማደስ እንዲነሳሳ ይጠቅማል ያልነውን ወሳኔ አሳልፈናል።
 • ምን ወሰናችሁ?
 • ቤት ለሌለው አመራር ቤት እንዲሰጥ ቤት ላለው ደግሞ…
 • እሺ… ቤት ላለው ምን?
 • ቤቱን የሚያድስበት ወጪ በአስተዳደሩ እንዲሸፈን ወስነናል።
 • ወሰናችሁ?
 • አዎ። ከዚህ በኋላ የአቅመ ደካሞችን ቤት ላለማደስ ማቅማማት አይችሉም፣ ምክንያትም አይኖራቸውም።
 • እኔም ሳላቅማማ አድሰዋለሁ!
 • ምኑን?
 • ካቢኔውን!

[የከተማ አስተዳደሩ ኃላፊ ከስብሰባው ከወጡ በኋላ ወደ ሚኒስትሩ ስልክ ደወሉ]

 • ክቡር ሚኒስትር ቅድም የተናገሩት የምርዎትን እንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ?
 • የሕዝብ ሀብት እየባከነ እንዴ እቀልዳለሁ?
 • ክቡር ሚኒስትር ሀብት እያባከንን አይደለም።
 • ታዲያ ሌላ ምን ሊባል ነው?
 • ቅድም ብቻዎትን ስላልነበሩ ተቆጥቤ እንጂ ምክንያቱ ሌላ ነው።
 • ሌላው ምክንያት ምንድነው?
 • ክቡር ሚኒስትር እኔ ፍርኃት አለኝ፣ ሥጋት አለኝ!
 • የምን ሥጋት?
 • አመራሩ ልቡ ሸፍቷል የት ቦታ እንደቆመ አይታወቅም። ይኼ አስፈርቶኛል።
 • ስለዚህ?
 • ሥጋት ስላለኝ ነው ፈጥኜ እስከ ወረዳ ያለውን አመራር በጥቅማ ጥቅም ለመያዝ የወሰንኩት።
 • እንደዚያ ነው?
 • አዎ። ፍርኃት ስላለኝ ነው። ሥጋት አለኝ።
 • እንደዚያ ከሆነ ገብቶታል ማለት ነው።
 • ምኑ?
 • ፕሮጀክቱ።
 • የቱ ፕሮጀክት?
 • የ90 ቀን!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...

ብሔራዊ ባንክ ጥርስ እያወጣ ይሆን እንዴ?

በአመሐ ኃይለ ማርያም ‹‹Better late than never›› (ከቀረ የዘገየ ይሻላል) የኢትዮጵያ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሐዘን ለመድረስ ጎረቤት ተገኝተው ለቀስተኛው በሙሉ የሚያወራው ነገር አልገባ ብሏቸው ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ባለቤታቸውን ስለጉዳዩ እየጠየቁ ነው] 

ጎረቤታችን ሐዘን ለመድረስ ብሄድ ለቀስተኛው በሙሉ በሹክሹክታ ያወራል። ግን የሚያወሩት ነገር ሊገባኝ አልቻለም። ምንድነው የሚያወሩት? እኔ ምን አውቄ? እንዴት? የሚያወሩትን ምንም አልተሰማሽም? እኔ እንድሰማ የፈለጉ አይመስልም ግን ... ግን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...