የሽግግር ፍትሕ ሥርዓትን ለመተግበር ይፋ በተደረገው የፖሊሲ ግብዓት ማሰባሰቢያ ሰነድ ውስጥ፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ቁርሾዎችን አግባብነት ባለው ሁለንተናዊ፣ አሳታፊና በተቀናጀ መንገድ፣ ሳይፈቱ ሲንከባለሉ የመጡ የሚባሉ በደሎችና ቁርሾዎች እንዲጠገኑና ወደ ተሻለ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሸጋገር ካስፈለገ፣ የሽግግር ፍትሕ ማስፈን አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ የተከናወኑ ኢፍትሐዊ የሆኑና በቁርሾ የተሞሉ ታሪኮችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመዝጋት፣ አዲሲቱን ኢትዮጵያ በአዲስና በተሻለ እሴት ለመገንባት ያሰበ መሆኑ ተብራርቷል፡፡
የፖሊሲ ግብዓት ለመሰብሰብ በተዘጋጀውና የአማራጭ አቅጣጫዎችን የያዘው ይህ የሽግግር ፖለሲ ሰነድ፣ ‹‹የሽግግር ፍትሕ ሒደት ከየትኛው ጊዜ ይጀምር?›› የሚል የተለያዩ አማራጭ ሐሳቦችን የያዘ ነው፡፡ ሒደቱ የሚሸፍናቸውን የጊዜ መነሻና መድረሻ ስለመወሰንም ያብራራል፡፡ በዚህም ሒደቱ ‹‹ከ1983 ዓ.ም. በፊት ወይም ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ፣ ወይም ከ1987 ዓ.ም. ወዲህ ያለው፣ ወይም ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ይሁን›› የሚሉ የተለያዩ አማራጮችን ከፋፍሎ አስቀምጧል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን በዚህ ሊንክ ይመልከቱ፡፡https://www.ethiopianreporter.com/116644/