ኢትዮጵያ በወራሪው የጣሊያን ሠራዊት ላይ በዓድዋ ድል የተቀዳጀችበት የየካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. 127ኛ ዓመት በአገር አቀፍ ደረጃ ተከብሯል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ በንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ሐውልት ሥር ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዱ ጉንጉን አበባ አስቀምጠዋል፡፡ በመንግሥታዊ አከባበርም የመከላከያ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ወታደራዊ ሠልፍም በመስቀል አደባባይ ተከናውኗል፡፡ ፎቶዎቹ የአከባበሩን ገጽታ ያሳያሉ፡፡