Thursday, March 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ የተጣለው ገደብ የመገናኛ ብዙኃን ሥራቸውን በአግባቡ ለሕዝብ ተደራሽ እንዳያደርጉ...

‹‹በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ የተጣለው ገደብ የመገናኛ ብዙኃን ሥራቸውን በአግባቡ ለሕዝብ ተደራሽ እንዳያደርጉ እንቅፋት በመሆኑ ገደቡ ሊነሳ ይገባል›› የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት

ቀን:

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግሥት በአንዳንድ የኢንተርኔት የግንኙነት መተግበሪያዎች ላይ የጣለው ገደብ፣ መገናኛ ብዙኃን በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን መረጃ የማሰባሰብ፣ የማደራጀትና ለሕዝብ ተደራሽ የማድረግ መብት ላይ ተግዳሮት መፍጠሩን መገንዘቡን ገልጾ ገደቡ እንዲነሳ አሳሰበ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኃን ባሳራጨው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የመገናኛ ብዙኃን የሰበሰቡትን መረጃ በአገርና በውጭ አገር ለሚገኙ ተደራሲያን ኢንተርኔትን እንደ ዋነኛ የመረጃ ማሰራጫ የሚጠቀሙ ቢሆንም፣ ሥራቸውን በአግባቡ ለማከናወን መቸገራቸውን ለምክር ቤቱ አቤቱታ እያቀረቡ ነው፡፡

በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238 በግልጽ እንደተመለከተው፣ የበይነ መረብ ጋዜጠኞችና ፈቃድ ያለው ማንኛውም የሚዲያ ተቋም ተመዝግቦ ሕጋዊ ሰውነት እስካገኘ ድረስ፣ በመደበኛው መገናኛ ብዙኃንና በበይነ መረብ  የሚተገበሩ የአገልግሎቶች መድረክ ወይም ፎርማት  (ድረ ገጽ፣ ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ሊንክዲን፣ ወዘተ) ሁሉንም ሙያዊ ሥነ ምግባርና የጋዜጠኝነት ዋና እሴቶችን እስካከበሩ ድረስ ገደብ ሊጣልባቸው እንደማይገባ አስረድቷል፡፡

በመሆኑም ሰሞኑን  በአገሪቱ ከተፈጠረው ሃይማኖታዊ አለመግባባቶች ጋር በተያያዘ  የችግሩን ስፋትና ክብደት ከግምት በማስገባት ሊቀለበስ የማይችል አደጋን ምክንያት በማድረግ ካልሆነ በስተቀር፣ ሕግን መሠረት በማድረግ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ መንግሥት ገደብ ሊያደርግ  እንደማይገባ እምነቱ መሆኑንም ምክር ቤቱ ጠቁሟል፡፡ 

ከዚህ አንፃር በአንዳንድ የኢንተርኔት መረጃ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎች ላይ የተጣለው ገደብ ሦስት ሳምንታትን ያስቆጠረ ከመሆኑም በላይ፣ ገደቡ የተደረገበትን ምክንያት የሚመለከተው መንግሥታዊ አካል የሰጠው ግልጽ ማብራሪያ አለመኖሩ፣ የተፈጠሩ ክስተቶችን ከሕግ ውጩ ሊያባብሱና ግጭት ለመቀስቀስ የሚጥሩ አንዳንድ የበይነ መረብ መገናኛ  ብዙኃንን  እንኳ በሕግ አግባብ ተጠያቂ ከማድረግ በዘለለ፣ የጠቅላላ ሕዝቡን መረጃ የማግኘትና የማሰራጨት መብት ላይ ገደብ ለመጣል የሚያበቃ አማራጭ እንዳልሆነ ምክር ቤቱ እንደሚያምን አስታውቋል፡፡

በተለይ ለዓመታት ለኅብረተሰቡ አማራጭ የመረጃ ምንጭ ሆኖ የዘለቀው የኅትመት መገናኛ ብዙኃን ከወረቀት ዋጋ መናርና ከኅትመት መወደድ ጋር በተያያዘ ከገበያ ውጪ በሆኑበት በዚህ ወቅት፣ ኢንተርኔትን አማራጭ የመረጃ ማስተላላፊ መንገድ አድርገው አገልግሎት እየሰጡ ባሉ የሚዲያ ተቋማት ላይ የፈጠረው ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ፣ መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ የጣለው ገደብ፣ የመገናኛ ብዙኃን ሥራቸውን በአግባቡ ለሕዝብ ተደራሽ እንዳያደርጉ እንቅፋት በመሆኑ ገደቡ ሊነሳ ይገባል ብሏል፡፡

በሌላ በኩል ማንኛውም መደበኛም ሆነ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን የሚያሰራጩዋቸው መረጃዎች በኅብረተሰቡ መካከል  የእርስ በእርስ ግጭት ማነሳሳት፣ የሌሎችን መብት ወይም እምነት ማንኳሰስ፣ ወይም በሃይማኖት ተከታዮች መካከል አለመቻቻል እንዲፈጠር መቀስቀስ እንደማይፈቀድ የተደነገገ በመሆኑ፣ የመገናኛ ብዙኃን ማንኛውንም መረጃ  በሚያሰራጩበት ወቅት በከፍተኛ ጥንቃቄ፣ በኃላፊነት መንፈስና ከፍ ባለ የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር በመመራት ሊሆን እንደሚገባ በአጽንኦት አሳስቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...