ኢትዮጵያ ከ127 ዓመታት በፊት የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም.የነጩን ዓለም ያናወጠ፣ ለጥቁር ሕዝቦች ሞገስ የሆነውን የዓድዋ ጦርነት በጣሊያን ወራሪ ሠራዊት በድል የተወጣችበት ዕለት ነበር፡፡ ይህንን የ19ኛው ምዕት ዓመት ታሪካዊ ገድል ነበር ጆርጅ በርክሌ በመጣጥፉ ያንፀባረቀው፡፡ ጆርጅ በርክሌ አያይዞም፣ 25,000 ሰዎች በአንድ ቀን ጀንበር የሞቱበትና የቆሰሉበት ነው፡፡ ፖለቲካና ታሪክ አበቃ ሲል ከትቦታል፡፡