Friday, March 31, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል አለ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል አለ

ቀን:

በሕገወጥ ደላሎች አማካይነት የተስፋፋው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በሕገወጥ ደላሎች አማካይነት ወደ ሌላ አገርም ሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ከከተማ ወደ ከተማ የሚደረግ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን፣ የኮሚሽኑ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰው በደላሎች አማካይነት የሚንቀሳቀሱ ሰዎች በተለያዩ አደጋዎች ሕይወታቸው እያለፈ፣ በሱስ እየተጠመዱና በወንጀል ድርጊት ውስጥ እየተገኙ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ኮማንደር ማርቆስ በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እየደረሰ ያለውን ችግር ሲያስረዱም፣ አገር አቋርጠው የሚጓዙ በርካታ ወጣቶች ዓላማቸው ሠርተው ራሳቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውን አገራቸውን መለወጥ ቢሆንም፣ በሕገወጥ ደላሎች አማካይነት ተገፍተው ከአገር ሲወጡ በባህር ውስጥ ሕይወታቸው እያለፈ ነው ብለዋል፡፡

 ወደ ሌሎች አገሮች ከሚደረገው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር በተጨማሪ፣ በአገር ውስጥም ከክልል ወደ ክልል ችግር እየተስፋፋና ችግር እያስከተለ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዜጎች ከተለያዩ የገጠር አካባቢዎች በሕገወጥ ደላሎች አማካይነት ወደ ከተማ አቅንተው በተሽከርካሪ አደጋ ሕይወታቸው በተለያዩ ሱሶች እንደሚጠመዱ፣ ራሳቸውንና ልጆቻቸውን ለአደጋ እንደሚያጋልጡ፣ እንዲሁም የአካል ጉዳት የሚደርስባቸው በርካታ ወጣቶች በአዲስ አበባ ከተማ እየተስተዋሉ መሆኑን የሕዝብ ግንኙኘት ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

ከአንዱ ወደ ሌላው ከተማ የሚደረግ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ሲያብራሩም፣ በርካቶች ከራሳቸው አልፈው ቤተሰቦቻቸውን ሊረዱበት የሚችሉ ጥሩ ሥራ በከተማ እንዳለ ደላሎች እንደሚያሳምኗቸው፣ ወደ ከተማ ከመጡ በኋላ ግን ያልጠበቁት ነገር ስለሚያጋጥማቸው በተለይ ግንዛቤ የሌላቸው ሰዎች በአንድ ቤት ውስጥ ተቀጥረው ለረጅም ዓመታት ጉልበታቸው እየተበዘበዘ እንደሚኖሩ ገልጸዋል፡፡

ከደላሎች ግፊት ባለፈም በራሳቸው ፍላጎት ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመምጣት ያሰቡት አልሳካላቸው ሲል በተለያዩ ሱሶች ከመጠመድ ባሻገር፣ ወንጀል የሚፈጸምባቸውና የሚፈጽሙ በመሆናቸው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲሉ ኮማንደር ማርቆስ ተናግረዋል፡፡

በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር በርካታ ችግሮች እየደረሱ መሆኑን ጠቅሰው፣ ወንጀል አስፈጻሚዎች ጎዳና ላይ ያሉ ሕፃናትንና ወጣቶችን በሕገወጥ ድርጊት እያሰማሯቸው መሆናቸውንም አክለው ገልጸዋል፡፡

ሰዎች ከአንዱ ክልል ወደ ሌላ ክልል ቢንቀሳቀሱ አልጋ በአልጋ የሆነ ሕይወት እንደሚኖራቸው የሚያሳምኑ፣ በሕገወጥ መንገድ የተሰማሩ ደላሎችና ተባባሪዎች፣ በፖሊስ ተይዘው ሕጋዊ ዕርምጃ እየተወሰደባቸው ነው ብለዋል፡፡

ዕርምጃ የተወሰደባቸው የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተሳታፊዎች ምን ያህል እንደሆኑ የተጠየቁት ኮማንደር ማርቆስ፣ ቁጥራቸውን ለመጥቀስ የተሰባሰበ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ በርካታ ምክንያቶች እንዳሉ ‹‹የተለያዩ መዛግብት ያስረዳሉ›› ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፣ ‹‹ሰዎች በትዳር መፍረስ ምክንያት ከአንድ ወደ ሌላ አካባቢ የሚሄዱበት አጋጣሚ አለ፤›› ብለው፣ ‹‹ሕፃናት በእንዲህ ዓይነት ችግር የሚበተኑበት አጋጣሚ እንዳለም ይታወቃል፤›› ብለዋል፡፡ 

‹‹ጦርነት፣ ረሃብና የተለያዩ ማኅበራዊ ችግሮች መፈጠራቸው ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ምክንያት ናቸው፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡  

‹‹የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የሚያከናውናቸው ሥራዎች በጣም ባርካታ ናቸው፡፡ በዋነኛነት የከተማው ሰላምና ደኅንነት በማረጋገጥ ማኅበረሰቡ ሰላም ወጥቶ እንዲገባ ከወንጀል መከላከል፣ ከትራፊክ አደጋ መከላከልና በምርመራ ሥራዎች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እየተሠራ ቢሆንም፣ ማኅበረሰቡም ሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪ ደላሎችን ሊያጋልጥ ይገባል፤›› በማለት አሳስበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...