Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅረቂቅ ድርሰቱ ከወህኒ ቤት ያስለቀቀው ደራሲ

ረቂቅ ድርሰቱ ከወህኒ ቤት ያስለቀቀው ደራሲ

ቀን:

ደራሲው የተወለደው በ 1936ዓ.ም በጌቾ ሰባት ቤት ጉራጌ ነው፡፡ በብዙ ችግርና መከራ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱ ከዳር አድርሷል፡፡ ከዚያም በፖሊስ ሠራዊት ውስጥ ገብቶ ከተራ ወታደርነት እስከ መቶ አለቃነት መዕረግ በመድረስ ከሃያ ዓመታት በላይ እንዳገለገለ ይነገራል፡፡

በአስራ ዘጠኝ ስድሳዎቹ መጨረሻ በኢትዮጵያና ሱማሌ መካካል በተደረገው ጦርነት ከተሳተፈ በኋላ በ1971 ዓ.ም እስከዛሬም ግልፅ ባልሆነ ምክንያት ሐረር ወህኒ ቤት ወረደ፡፡

አንግዲህ እዚህ እስር ቤት እያለ ነበር መጫጨር የጀመረው፡፡ወረቀት ስለማይገባ በሲጋራ ፓኮ ላይ ነበር ሲጽፍ የነበረው፡፡ እናም በዚህ የሲጋራ ፓኮ ላይ የጀመረውን ድርሰት አጠናቆ ለኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ላከ፡፡ አሳታሚ ድርጅቱም ረቂቁን ድርሰት ስለወደደው አንዳንድ ማስተካከያ ለማድርግ ደራሲውን ለማነጋገር ስለፈለገ አስጠራው፡፡ ይሁን እንጂ ለአሳታሚ ድርጅት የመጣው መልዕክት አስደንጋጭ ነበር “ደራሲው እስር ቤት ስለሆነ መምጣት አይችልም” የሚል፡፡

አሳታሚው ድርጅት ወዲያውኑ ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋግሮ ደራሲውን አስፈታውና መጽሐፉም ታተመ፡፡

መጽሐፉ በታታመ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በአንባቢያ ዘንድ እጅግ በጣም ተወዳጅ ሆነ፡፡ የዚህ ተወዳጅ መጽሐፍ ደራሲ ገበየሁ አየለ ሲሆን፣ ከወህኒ ያስፈታው መጽሐፍ ደግሞ “ጣምራ ጦር” ይሰኛል፡፡

ደራሲ ገበየሁ አየለ ከዚህች መጽሐፍ ኅትመት በኋላ ስደተኛው፣ እንባና ሳቅ የተሰኙ ወጥ ልቦለዶችን ያሳተመ ሲሆን፣ “ረመጥ” የተሰኘ ታሪካዊ ልቦለድ ደግሞ ከቀኝ አዝማች ታደሰ ዘወልዲ (ቀሪን ገረመው) ጋር በጋራ ለንባብ አብቅቷል፡፡

ደራሲ ገበየሁ አየለ ከዚህም ሌላ ከሌሎች ደራሲያን ጋር አጫጭር ልቦለዶችን በእነሆ፣ በአባ ደፋር፣ በሕይወት ጠብታዎች እና በክንፋም ህልሞች መድበሎች ውስጥ እስነብቦናል፡፡

ደራሲው እ.ኤ.አ በ2011 በኮድ ኢትዮጵያ ለሽልማት የበቃ escape የተሰኘ ድርሰትም በእንግሊዘኛ ቋንቋ ጽፎ ለንባብ አብቅቷል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ደራሲው በልጆች መጽሐፍም ከፍተኛ አበርክቶት አለው፡፡ ለልጆች ካበረከታቸው መጽሕፍት መሃል፡ አረንጓዴው ቡድን፣ በድሉ በረኛው፣አዴ ሜዳ፣ ቢራቢሮና አበባ፣ ጥንቸሉ ጴጥሮስ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በነገራችን ላይ የጥንቸሉ ጴትሮስ መነሻ ሀሳብ የተገኘው እኔን ጨምሮ መላው ዓለም ከሚያደንቃት ከቢትርክስ ፖተር Peter Rabbit ከተሰኙ ተከታታይ ድርሰቶቿ ነው፡፡

በአሁን ሰዓት የሦስት ልጆች አባትና የ79 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ የሆነው አንጋፋው ደራሲ፣ ጋቢውን ትከሻው ላይ ጣል አድርጎ ሻዩን ፉት እያለ፣ ትናንት ካለፈበት ከሕይወት ጎዳና በሰፊው እየቀዳ አሁን ከሚያያው፣ ካነበበውና ከታዘበው የሕይወት ምዕራፍ ጨለፍ እያደረገ ለነገው ትውልድ የተስፋን ችቦ ለማቀበል እየተጋ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

  • እንዳለ ገነቦ እንዳለ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሠፈረው
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...