Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየአፍሪካን የግብርና አቅም ለማሳደግ የተጠየቀው ዓለም አቀፍ ድጋፍ

የአፍሪካን የግብርና አቅም ለማሳደግ የተጠየቀው ዓለም አቀፍ ድጋፍ

ቀን:

በዓለም ለእርሻ አገልግሎት ይሆናሉ ከተባሉ ቦታዎች 65 በመቶ ያህሉ የሚኘው በአፍሪካ ነው፡፡ በአፍሪካ 70 በመቶ የሚሆነው ሕዝብም ኑሮው የተመሠረተው በግብርና ላይ መሆኑን የአፍረካ ኅብረት መረጃ ያሳያል፡፡

ሆኖም 65 በመቶ የሚታረስ መሬት የሚገኝባት አፍሪካ፣ በዓለም በግብርናው ከሚመረተው ምርት አሥር በመቶውን ብቻ ትሸፍናለች፡፡ የአፍሪካ ግብርናም በዝቅተኛ ምርታማነቱ እንጂ በአመርቂነቱ አይታወቅም፡፡

ዝቅተኛ የግብርና ኢንቨስትመንት፣ የሚወጡ ፖሊሲዎች በአብዛኛው ከተማ ነክ ጉዳዮች ላይ ማተኮራቸው፣ ዋስትና ያለው መሬት የማግኘት ችግርን ጨምሮ ሴቶች በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል ካፒታል አለማግኘታቸው ከዘርፉ ማነቆዎች ይመደባሉ፡፡

የአፍሪካ ግብርና ዝቅተኛ ዕሴት ያለውና ያልተሟላ መሠረተ ልማት ባሉባቸው ሥፍራዎች የሚከወን መሆኑም ለሕዝቡ መድረስ አልቻለም፡፡ ይልቁንም ረሃብ የአፍሪካውያን መለያ ሆኗል፡፡ ስለረሃብ ሲነሳም ቀድሞ የሚነሳው የአፍሪካ አኅጉር ነው፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ በዓለም በተለያዩ የድህነት ዓይነቶች ከተመቱ ሕዝቦች ውስጥ 456 ሚሊዮን ያህሉ በአፍሪካ ይገኛሉ፡፡

የግብርናው ዓላማ ዳግም ምርታማነት፣ የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት፣ ችግር ተቋቁሞ መኖር የሚያስችል ሥርዓትም ሆነ አቅም ማጎልበት ላይ የራሱን አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የአካባቢዎችና የተፈጥሮ ሀብቶች በተለያዩ ችግሮች የተተበተቡ መሆን፣ በተለይም አፋጣኝ ምላሽ የሚሻው የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ አለማግኘቱ የግብርናውን ምርታማነትም ሆነ የምግብ ዋስትናን ተገዳድረውታል፡፡

አኅጉሪቷ እየተፈራረቀ ከሚከሰተው ድርቅ፣ ረሃብና ጠኔ ለመውጣት የግብርናውን ምርታማነት ሊያሳድጉ የሚችሉ ፖሊሲዎች እንደሚያስፈልጓት የሚያሰምርበት ኅብረቱ፣ በተለይ ሕፃናት ላይ ያተኮሩ፣ አዋጭ የተመጣጠነ ምግብ ፖሊሲዎች ማውጣት፣ የቤተሰብ የምግብ ዋስትና ችግር ሲጋጥማቸው የሚወጡበትን አቅም መገንባት፣ ሴቶችን ማበልፀግ፣ አካል ጉዳተኞችን መድረስና የገጠር መሠረተ ልማትን ማፋጠን ግድ የሚሉ ጉዳዮች ናቸው ብሏል፡፡

የአፍሪካን ግብርና ለማሳደግና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽነትን ለማረጋጋት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ከሪጅናል ኢኮኖሚክ ኮሙዩኒቲስ (አርኢሲ) እንዲሁም ከኒው ፓርትነርሽፕ ፎር አፍሪካስ ኤቨሎፕመንት ኮኦርዲኔቲንግ ኤጀንሲ (ኤንፒሲኤ) ጋር በመተባበር ምርታማነትን ለማሳደግና ተደራሽ በማድረግ አፍሪካ ራሷን እንድትመግብ፣ የግብርና ምርትን እንድትልክ እንዲሁም በድርቅ ምክንያት እየተባባሰ የመጣውን የምግብ ቀውስ ለመቀነስ እየሠራ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ የተካሄደው 36ኛው መደበኛ የመሪዎች ስብሰባ አጀንዳ አድርጎ ካነሳቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱም የአፍሪካን ግብርና አፍሪካውያንን እንዲመግብ ማስቻል ነው፡፡ በመሆኑም የአፍሪካን የግብርና አቅም ለማሳደግ ዓለም አቀፍ ረጂዎች ባለፈው ወር የገቡትን የገንዘብ ድጋፍ ቃል እንዲተገበር ኅብረቱ ጠይቋል፡፡

በጥር 2015 ዓ.ም. በሴኔጋል ዳካር በተደረገው የአፍሪካ ሁለተኛው የምግብ ጉባዔ የአፍሪካ የልማት አጋሮች በአፍሪካ የግብርና ምርትን ለማሳደግና አኅጉሪቷን የዓለም የዳቦ ቅርጫት ለማድረግ የገቡትን የ30 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ተግባራዊ እንዲያደርጉ የአፍሪካ ጉባዔው ሲጠናቀቅ መሪዎች በሰጡት መግለጫ አስታውሰዋል፡፡

የአፍሪካን ግብርና ለማሳደግ በሴኔጋል ዳካር በተደረሰው ስምምነት መሠረት የአፍሪካ ልማት ባንክ በአምስት ዓመታት ውስጥ 10 ቢሊዮን ዶላር፣ እስላሚክ ልማት ባንክ አምስት ቢሊዮን ዶላር ለመደገፍ መስማማታቸው ይታወሳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የኔዘርላድስ ዓለም አቀፍ ትብብር በቀጣይ አምስት ዓመታት በተለይ ከሰሃራ በታች ለሚገኙ አገሮች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ 450 ሚሊዮን ዩሮ ለመለገስ ቃል ገብታለች፡፡

ይህንን ሌሎ ግብርናውን ለማዘመን የሚሰሩ ሥራዎችን አካቶ ‹‹አፍሪካን መመገብ፣ የምግብ ልዕልናና ችግርን መቋቋም›› በሚል ድንጋጌ ተዘጋጅቶም የዳካሩ ጉባዔ ለአፍሪካ ኅብረት በተላከው መሠረት፣ በ36ኛ መደበኛ ጉባዔው ኅብረቱ ይህንን አጀንዳና አጋር ድርጅቶች የገቡትን ቃል ተቀብሎ ተፈጻሚ እንዲሆን ወስኗል፡፡

የአፍሪካ መሪዎችም የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽንና የአፍሪካ ልማት ባንክ የተለያዩ የልማት አጋሮች የአፍሪካን ግብርና ለመደገፍ የተስማሙበትን የ30 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍና ኢንቨስትመንት ዕውን ማድረጋቸውን ተከታትለው ለ2016 ዓ.ም. ጉባዔ ሪፖርት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹ከኦነግ ሸኔ ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት አለን›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ

መንግሥት ከ‹‹ኦነግ ሸኔ››ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት...

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...