Friday, March 31, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ቻይና ላላደጉ አገሮች በምትሰጠው የታሪፍ ነፃ ዕድል ኢትዮጵያ ተካተተች

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ያላደጉ አገሮች ምርቶቻቸውን ወደ አገሯ ከታሪፍ ነፃ በሆነ ገበያ እንዲያስገቡ መፍቀድ ጀምራ የነበረችው ቻይና፣ እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 1 ቀን 2023 ጀምሮ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሦስት የአፍሪካ አገሮችን በዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መፍቀዷ ታወቀ፡፡  

ወደ ቻይና ገቢ ከሆኑና ቀረጥ ከሚጣልባቸው ምርቶች 98 በመቶ የሚሆኑትን ከታሪፍ ነፃ በሆነ መንገድ እንዲያስገቡ የሚፈቅደውን ዕድል የቻይና መንግሥት ያላደጉ አገሮች እንዲጠቀሙበት ፈቅዶ የነበረ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ታኅሳስ 1 ቀን 2022 የመጀመርያው ዙር ከተፈቀደላቸው አሥር የአገሮች ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ አልተካተተችም ነበር።

ሆኖም ግን ባለፈው ሳምንት የቻይና መንግሥት በተጨማሪ እንዲካተቱ ከፈቀደላቸው ሦስት አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ ሆናና 8,804 የምርት ዓይነቶች ከታሪፍ ነፃ ተጠቃሚ እንድንሆን ፈቅዳለች። ቡሩንዲና ኒጀር ሁለቱ በተጨማሪ እንዲካተቱ የተፈቀደላቸው አገሮች ናቸው። ከአንድ ዓመት በፊት የዓለም ምጣኔ ሀብት እንዲበረታታ በማለም የቻይና መንግሥት አዲስ ፖሊሲ አውጥቶ ያላደጉ አገሮች መንግሥታት ውል እየገቡ የሚልኩትን ምርቶች ዝርዝር ሲያፀድቅ ነበር።

የቻይና መንግሥት መረጃ ቢሮ የአገሪቱን የጉምሩክ ታሪፍ ኮሚሽን መሥሪያ ቤት ጠቅሶ ባለፈው ሰኞ የካቲት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ያወጣው መረጃ እንደሚገልጸው፣ ያላደጉ አገሮች ዕድገታቸውን እንዲያፋጥኑና ለዓለም ቅርብ የሆነ ምጣኔ ሀብት እንዲያዳብሩ በማለም ውሳኔውን እንዳሳለፈ ነው። ከቻይና ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላቸው ሌሎችም ያላደጉ አገሮች በዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድሉን እያሰፉ እንደሚሄዱም አክለው በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

በታኅሳስ ወር ዕድሉ ከተሰጣቸው አሥሩ አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ ያለመካተቷን ሪፖርተር ከዚህ ዘግቦ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ምክንያቱም ኢትዮጵያ አዘጋጅታ ማቅረብ የነበረባትን ሰነድ በጊዜው ባለማስገባቷ ነበር። በጊዜው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከታሪፍ ነፃ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ዝርዝር ምርቶችን ከቻይና ኤምባሲ አግኝቶ የነበረ ቢሆንም፣ ሚኒስቴሩ በአፋጣኝ ለኤምባሲው ባለመላኩ እንደዘገየም መዘገቡ ይታወሳል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች