ከሰማንያ ስድስት ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የፋሺስት ጣሊያን ጭፍራዎች ከየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. አንስቶ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ባደረጉት ፍጅት፣ 30 ሺሕ ኢትዮጵያውያን ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡ የሰማዕታቱ መታሰቢያ ስድስት ኪሎ በሚገኘው ሐውልታቸው ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. እየታሰበ ነው፡፡ ከስድስት ዓመት በፊት ዕለቱ ሲታሰብ ከተገኙት አንዱ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን (ከቀኝ 4ኛው) ‹‹ጀግኖች አልፈዋል፣ ታሪካቸው፣ አልነካ ባይነታቸውና ልዕልናቸው ግን አያልፍም፤›› ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ፎቶው የያኔውን አከባበር ያሳያል፡፡