Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየወልቂጤ ፖሊስ በወሰደው ተመጣጣኝ ያልሆነ ዕርምጃ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

የወልቂጤ ፖሊስ በወሰደው ተመጣጣኝ ያልሆነ ዕርምጃ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

ቀን:

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች፣ የቧንቧ ውኃ አቅርቦት ከወር በላይ ለሆነ ጊዜ መቋረጡን ተከትሎ ሠልፍ በወጡ ዜጎች ላይ ፖሊስ በወሰደው የኃይል ዕርምጃ፣ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ዜጎች ላጋጠማቸው የውኃ ችግር መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ለማቅረብ ሠልፍ በወጡ ነዋሪዎች ላይ በፖሊስ በተወሰደ የኃይል ዕርምጃ በነዋሪዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን አስታወቋል፡፡

 ኮሚሽኑ የዓይን ምስክሮችን፣ ተጎጂዎችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችንና የጤና ባለሙያዎችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ሪፖርት ጭንቅላታቸውና ደረታቸው ላይ በጥይት ተመተው ከተገደሉት በተጨማሪ ቢያንስ በ30 ሰዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው የአካል ጉዳት መድረሱን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ይሁን እንጂ የአካባቢው ባለሥልጣናት በበኩላቸው ለደረሰው ጉዳት ምክንያት የሆነው ከሠልፈኞች ውስጥ የተወሰኑት ሰዎች የከተማው የውኃ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ላይ ድንጋይ መወርወራቸውንና የመኪና መንገድ መዝጋታቸውን ተከትሎ በክልሉ ፖሊስ በተወሰደ የኃይል ዕርምጃ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የተወሰደው የኃይል ዕርምጃ ከተፈጠረው ጉዳይ አንፃር ተመጣጣኝ ያልሆነ መሆኑንና ‹‹አንገብጋቢ በሆነ የውኃ አቅርቦት ጥያቄ ሠልፍ ወጥተው ድንጋይ በወረወሩና መንገድ በዘጉ ሰዎች ላይ፣ ሕይወት የሚያጠፋ መሣሪያ ተጠቅሞና ጥይት ተተኩሶ ነዋሪዎች መገደላቸው ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ዕርምጃ መሆኑነን የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በመግለጫው አስታውቀዋል፡፡

ኮሚሽነር ዳንኤል (ዶ/ር) የክልሉ መንግሥት አስቸኳይ ማጣራት አድርጎ በአጥፊዎች ላይ ተጠያቂነት ሊያረጋግጥና የተጎዱ ሰዎችም ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ በማሳሰብ፣ ለወደፊቱም ተመሳሳይ ዓይነት የመብት ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ ለፀጥታ ኃይሎች ግልጽ አመራር እንዲተላለፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...