Thursday, March 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአፍሪካ ዲፕሎማሲ ካውንስል ተመሠረተ

የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ካውንስል ተመሠረተ

ቀን:

ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔን ማምጣት ዓላማው ያደረገና ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ በሰላምና ፀጥታ ላይ ያሉ ባለሙያዎችንና ወጣት ዲፕሎማቶችን ያካተተ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ካውንስል በይፋ ተመሠረተ፡፡

36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ አዲስ አበባ ላይ እየተካሄደ ሲሆን፣ ከዚያ ጎን ለጎን የአፍሪካ የሰላምና ፀጥታ ኅብረት (African Peace and Security Union-APSU) በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ቀናት የቆየ ኮንፍረንስ አካሂዷል፡፡

የኮንፍረንሱ ዋና አጀንዳም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እንዲሁም የግል ዘርፉ በአኅጉራዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ምን አስተዋፅኦ አላቸው? በሚል ርዕሰ ሐሳብ ላይ ከተለያዩ አገሮችና አኅጉሮች ከተወጣጡ የሰላምና ፀጥታ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ኮንፍረንስ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በኮንፍረንሱ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ካውንስል በይፋ ተመስርቷል፡፡ ካውንስሉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን፣ በሰላምና ፀጥታ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን እንዲሁም ወጣት ዲፕሎማቶችን ያካተተ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄን ለማምጣት በማሰብ የተቋቋመ መሆኑ ዓርብ የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በካሲዮፒያ ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ላይ ተገልጿል፡፡

ከአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ጎን ለጎን በተደረገው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ሰላምን ሁኔታ ላይ የሚመክር ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ ከፍተኛ ውጤት እንደተገኘበት፣ የአፍሪካ የሰላምና ፀጥታ ኅብረት (African Peace and Security Union-APSU) ሰብሳቢ የሆኑት ሮል ሴቴፋኒ ገልጸዋል፡፡

ሮል ሴቴፋኒ እንዳስረዱት፣ ለሁለት ቀናት በቆየው ሁነት ከተገኙ ጉዳዮች ውስጥ፣ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ካውንስል ምሥረታ ይፋ መደረግ አንዱ እንደሆነ ገልጸው፣ በዚህም የአፍሪካ ባለሙያዎችን (ኤክስፐርቶችን) በማሰባሰብ በአኅጉሪቱ ሰላምና ዲፕሎማሲ የማስተዋወቅ ሥራ የሚሠራ ይሆናል፡፡

ሰላምና ፀጥታ መሠረት አድርጎ በተካሄደው ኮንፍረንስ የሲቪል ማኅበረሰቡ፣ ወጣቱ፣ ሴቶች ምን ሚና አላቸው በተለይም የግሉ ዘርፍ ለሰላም ግንባታ ምን ሚና አላቸው የሚሉት ጉዳዮች ዘለግ ያለ የውይይት ጊዜ መውሰዳቸው ተጠቅሷል፡፡

ሰላም ሲመጣ ዲፕሎማሲ አስገፈላጊ መሆኑ ተጠቅሶ ከዚህ በተጨማሪ ስለ ሰላም በተለያዩ የአፍሪካ አኅጉሮች ተንቀሳቅሰው ወጣቱና ማኅበረሰቡን የሚያነቁ የፓን አፍሪካ የሰላም አምባሳደሮች ምርጫ መደረጉ ይፋ ሆኗል፡፡

ከየካቲት 9 እስከ 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በነበሩት ውይይቶች በተለይም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ በአኅጉሪቱ ውስጥ ቀልጣፋ (ፈጣን) ለኅብረተሰቡ ግልጋሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆን እንዳለባቸው መገለጹን ያስታወቁት የፓን አፍሪካ የሰላም አምባሳደር በመሆን የተመረጡት ሳማንታ ሲሚዮን፣ በአኅጉሪቱ በርካታ የሲቪል ማኅበረሰብ ደርጅቶችና የግል ተቋማት ቢኖሩም ሕዝቡን ለማገዝ የተጠበቀውን ያህል አለመንቀሳቀሳቸውን ጠቅሰዋል፡፡

አንዱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በተጠበቀው ልክ እንዳይንቀሳቀሱ ያደረጋቸው ነገር በገንዘብ ያለመደራጀታቸው መሆኑ ተገልፆ፣ የግሉም ዘርፍ እንዲሁ ከሲቪል ማኅበረሰብ ደርጅቶ ጋር መቀናጀትና ዘላቂ መሠረት ያለውና ራሱን ችሎ መንቀሳቀስ የሚችል ጥምረት መፍጠር እንደሚገባቸው ሳማንታ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...