Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየቀድሞው የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት የአፍሪካ የምግብ ሊቀ-መናብርትነትን ከፕሬዚዳንት ኦባሳንጆ ተረከቡ

የቀድሞው የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት የአፍሪካ የምግብ ሊቀ-መናብርትነትን ከፕሬዚዳንት ኦባሳንጆ ተረከቡ

ቀን:

የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ የአፍሪካ የምግብ ሽልማት ኮሚቴ ሊቀ-መንበርነታቸውን ለቀድሞው የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጃካያ ምሪሾ ኪክዌፔ በአዲስ አበባ ርክክብ አካሄዱ፡፡

የአፍሪካ የምግብ ሽልማት በአፍሪካ ውስጥ የግብርና እውነታውን ለመቀየር የሚደረገውን ጥረት የሚመራ የላቀ ግለሰብ ወይም ተቋም ዕውቅና የሚሰጥበት ሽልማት፡፡

የአፍሪካ አኅጉር ቀጣይነት ባለው ፈጠራና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ግብርናውን ለማሳደግ ለሚሠሩ ግለሰቦችና ተቋማት 100 ሺሕ ዶላር በየዓመቱ ሽልማት የሚያበረክተው፣ የአፍሪካ ግብርና ድርጅት (አግራ) ከ36ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ጎን ለጎን የርክክብ ሥነ ሥርዓቱን በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡

በአኅጉሩ ረሃብንና ድህነትን ለማስወገድና ወሳኝ አዲስ የሥራና የገቢ ምንጭ ለማቅረብ የተሻለ የግብርና ፈጠራ ላሳዩ ግለሰቦች የሚሰጠው ሽልማቱ በ2005 እ.ኤ.አ የተጀመረ ሲሆን፣ ከተጀመረ ጀምሮ የቀድሞ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሥራ አሰፈጻሚ ኢሌኒ ገብረ መድህን (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች ከኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ዩጋንዳ፣ ናይጄሪያ፣ ማላዊ፣ ሴኔጋል፣ ዚምባቡዌ፣ ታንዛኒያና ሞዛምቢክ የተመረጡ አፍሪካውያንን ሸልሟል፡፡

  በፕሮግራሙ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአፍሪካ የግብርና ድርጅት (አግራ) የቦርድ ሊቀ መንበር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ እንዲሁም የቀድሞው የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጃካያ ምሪሾ ኪክዌፔ ተገኝተዋል፡፡

የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ስለሽልማቱ ሲናገሩ፣ ሽልማቱ አፍሪካውያን የፈጠራ ባለሙያዎች አኅጉሪቷ ድህነትን ለመዋጋትና ለመቀነስ በምታደርገው ጥረት ዕገዛ ለሚያደርጉ አካላት የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ባደረጉት ንግግር ‹‹ከእንግዲህ ግብርናን ማዘመንና መለወጥ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው›› ብለዋል፡፡ አኅጉሩ ወጣቶችንና የግሉን ዘርፍ ያሳተፈ ዘመናዊ የግብርና ኢንቨስትመንት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ኃይለማርያም የፖለቲካ አመራሩ በግብርናው ዘርፍ ላይ መዋቅራዊ ፍተሻዎችን ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡

አፍሪካ በምግብ ራሷን እንድትችል ምርታማና ትርፋማ እንድትሆን በመስራት ተቋሙ በዘርፉ ትልቅ አስተዋጽኦን ላበረከቱ አፍሪካውያን የሚሰጠው ሽልማት ከቅዳሜ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በዘርፉ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሰዎችን መጠቆም የሚቻል ሲሆን ለቀጣይ ሦስት ወራት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...