Friday, March 31, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልበማርች ባንድና በዘመናዊ ኦርኬስትራ የሠለጠኑ ከምረቃ በኋላ ወዴት ናቸው?

በማርች ባንድና በዘመናዊ ኦርኬስትራ የሠለጠኑ ከምረቃ በኋላ ወዴት ናቸው?

ቀን:

በአበበ ፍቅር

በዳግማዊ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከሚያዝያ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም. በማርችንግ ባንድና በዘመናዊ ኦርኬስትራ ሙዚቃ የሠለጠኑ 35 ተማሪዎች የካቲት 4 ቀን ተመርቀዋል፡፡

ተማሪዎቹ ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን ላለፉት አሥር ወራት የማርች ባንድ የሙዚቃ መሣሪያዎችንና የተለያዩ የሙዚቃ ሥልቶችን በንድፈ ሐሳብና በተግባር ሲሠለጥኑ ቆይተው መመረቃቸውን የማርች ባንዱ መሥራችና አሠልጣኝ ሌተናል ኮሎኔል ሲሳይ ፍቃዱ ተናግረዋል፡፡

በጡረታ ከሙያቸው የተገለሉት ሌተናል ኮሎኔል ሲሳይ በወታደር ቤት ቆይታቸው በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ በነበራቸው እንቅስቃሴ ያገኙትን ዕውቀት በመጠቀም በጡረታ ዘመናቸው ተማሪዎችን አሰባስበው ያለምንም ክፍያ ሲያሠለጥኑ እንደቆዩ ገልጸዋል፡፡

ላለፉት 40 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የዳግማዊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት  ቤት የማርች ባንድ ትምህርት ለምን ተቋረጠ? የሚለው የሁልጊዜ ጥያቄ የሆነባቸው ኮሎኔል ሲሳይ በውስጣቸው የሚመላለሰውን ጥያቄ ለመመለስ ምንም በሌለበትና ከኪሳቸው አውጥተው በገዙት የሙዚቃ መሣሪያ ተማሪዎችን አሰባስበው ማርቺንግ ባንዱን ለማስቀጠል እንደወሰኑ ተናግረዋል፡፡

በትምህርት ቤቱ አስተዳደር ቀናኢነት የማርቺንግ ባንዱን ሥልጠና እንዲሰጡ ፈቃድ ካገኙ በኋላ 110 ተማሪዎችን ለምልመላ በማቅረብ ሃምሳ ተማሪዎች ወደ ሥልጠና መግባታቸውንና ወደ ሥልጠና ከገቡት ሃምሳ ተማሪዎች መካከከል 35ቱ ለምረቃ ማብቃታቸውን ገልጸዋል፡፡  

በሙያቸው የራሳቸውን አሻራ ለማስቀመጥና ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ በራስ ተነሳሽነት የገቡበትና በሕይወታቸው ትልቅ መስዋዕትነት የከፈሉበት እንደሆነ አንስተው፣ ልፋታቸውም ወደ ገንዘብ ሲቀየር ከ700 ሺሕ ብር በላይ ሊያወጣ እንደሚችል ኮሎኔል ሲሳይ ተናግረዋል፡፡

‹‹የዳግማዊ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዘመናዊ ትምህርት የተጀመረበት ታሪካዊ ትምህርት ቤት መሆኑን ትውልዱ በደንብ ሊረዳ ይገባል፤›› ያሉት የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ሰብሳቢ አቶ አበረ፣ የመጀመሪያው ዘመናዊ ተውኔት የተጀመረው እዚሁ መሆኑን አንስተው፣ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፣ ሐዲስ ዓለማየሁ፣ በዓሉ ግርማና ሌሎች አንጋፋ የኪነ ጥበብ ሰዎችን ያፈራ ትምህርት ቤት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ የተመረቁ ተማሪዎችም የአንጋፋዎቹን የኪነ ጥበብ ሰዎች ፈለግ በመከተል በኪነ ጥበብ ዘርፍ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር በየክረምቱ የኪነ ጥበብ ፍላጎትና ዝንባሌ ላላቸው ተማሪዎች በተውኔት ዝግጅት፣ በግጥም አቀራረብ፣ በረዥምና አጭር ልቦለድ አጻጻፍና በመሳሰሉት የኪነ ጥበብ ዘርፎች በነፃ ትምህርትና ሥልጠና ለመስጠት ተቋማቸው ፈቃደኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

‹‹የልፋታችንን ውጤት ያየንበት ነው›› ያለቺው የማርቺንግ ባንዱ አባል በእምነት ሞገስ የክላርኔት ተጫዎች እንደሆነች ተናግራለች፡፡ የሙዚቃ ጥበብ በውስጧ እንዳለና በትምህርት ቤቷ ቀደም ብሎ በነበረው የኦርኬስትራ ክበብ አባል እንደነበረች በመካከሉ ኮሎኔል ሲሳይ በበጎ ፈቃድ ሙያቸውንና የማርቺንግ ባንድ ሙዚቃ መሣሪያቸውን በመጠቀም ሥልጠና እንደሚሰጣቸው ስትሰማ የተሰማት ደስታ ልዩ እንደነበር ተናግራለች፡፡

ወጣቷ ለህልሟ መሳካትና ለዚህ ምዕራፍ ለመድረስ ከኮሎኔል ሲሳይ ባሻገር በምፈልገው የሙያ ዘርፍ እንድሳተፍ የረዱኝ ወላጆቼ ናቸው ትላለች፡፡ ወላጆቿ ሙያዋን እንደሚያከብሩላትና ውጤታማ እንድትሆን እንደሚያበረታቷት የምትናገረው በእምነት ይህ የወላጆች ድጋፍና ክትትል በሁሉም የባንዱ አባሎች ላይ ይስተዋላል ብላለች፡፡

የክላርኔት ሙያዋን በማዳበር ነገ የተሻለ ደረጃ በመድረስ በዘርፉ የራሷን አሻራ ማስቀመጥ የወደፊት ህልሟ እንደሆነ የገለጸችው በእምነት፣ ህልሟን ለማሳካት ጠንክራ እንደምትሠራ ተናግራለች፡፡

የግል ሕይወታቸውን ወደ ጎን በማለት ገንዘብና ጊዜያቸውን መስዋዕት በማድረግ ያለምንም ክፍያ ለአሥር ወር ከተማሪዎች ጋር ጊዜያቸውን ያሳለፉት ሌተናል ኮሎኔል ሲሳይ ፍቃዱ፣ የተመራቂዎች ቀጣይ መዳረሻ የትነው? የሚለው ጥያቄ በእጅጉ እንደሚያሳስባቸው ሳይናገሩ አላለፉም፡፡

‹‹ሙያዬና አቅሜ የፈቀደውን ያህል እዚህ ካደረስኳቸው በቀጣይ ወደ ራሴ ኑሮ መመለስ እፈልጋለሁ›› ቢሉም፣ ጊዜዬንና ገንዘቤን በማውጣት የለፋሁባቸው ተማሪዎች ተመርቀው እንዲበተኑ ሳይሆን፣ ነገ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ብሎም አገራቸውን በኪነ ጥበብ ዘርፉ እንዲያስጠሩ ምኞቴ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ያሉት ኮሎኔል ሲሳይ ጅምሩን ለማስቀጠል በሁሉም የአዲስ አበባና የክልል ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፋ የመዲናÀቱ ትምህርት ቢሮ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሥራው የአንድ ተቋም ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም የኪነ ጥበብና የሌሎች ባለሙያዎች ትልቅ ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡ በተለይ ደግሞ በኪነ ጥበብ ዘርፉ ያሉ ባለድርሻ አካላት ማርች ባንዱ የራሱ የሆነ ገቢ ይኖረው ዘንድ ከፍተኛ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአደባባይ በትልቅ መድረኮችና በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ እየተገኙ ልዩ ልዩ ትርዒቶችን በማሳየት ሙያቸውንና ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር ሊያደርጉላቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ሌተናል ኮሎኔል ሲሳይ በቀጣይ የራሳቸው የሆነ ጠንካራ የማርች ባንድ ትምህርት ቤት ለማቋቋም በዝግጅት ላይ እንደሆኑ ተናግረው፣ አብሮ መሥራትና መደገፍ የሚፈልግ ባለሀብትና ባለሙያ ካለ ለመቀበል ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...