ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን ማነጋገራቸውን በትዊተር ገጻቸው ሲገልጹ ያሰፈሩት ኃይለቃል፡፡ በመንበረ ፓትርያርክ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር እሑድ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. የተወያዩት ፕሬዚዳንቷ፣ በማኅበራዊ ገጻቸው አክለው የገለጹት ኢትዮጵያ ባሏት ዘመናትን ያስቆጠሩ ባህሎች ሃይማኖቶቿ ታሪኳ… እንኮራለን፡፡ እንጠብቃቸው፣ ከጥቃት እንከላከላቸው በማለት ነው፡፡
ጥንቃቄ ብልሃት፣ ጥበብ፣ የሰከነ አዕምሮ፣ እርጋታ፣ አርቆ አስተዋይነት… የችግሮች መፍቻ ዘዴዎች ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንቷ፣ የሃይማኖት ጉዳይ የቤተ እምነቶቹ አባቶችና ምዕመናን ጉዳይ ነው ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል፡፡