ማፍቀር አይደለም
ድንቁ
እንጂ
አፍቅሮ ማፍቀርን ማወቁ
መፈቀር መች ሁኖ ብልሃቱ
እንጂ እውቀቱ
ሲፈቀሩ ፍቅር መሰማቱ
እውቀት አይደለም
ቁም ነገሩ
ጉዱ
እንዳወቁ ማወቁ
- ሰሎሞን ዴሬሣ ‹‹ዘበት እልፈቱ ወለሎታት›› (1950)
ማፍቀር አይደለም
ድንቁ
እንጂ
አፍቅሮ ማፍቀርን ማወቁ
መፈቀር መች ሁኖ ብልሃቱ
እንጂ እውቀቱ
ሲፈቀሩ ፍቅር መሰማቱ
እውቀት አይደለም
ቁም ነገሩ
ጉዱ
እንዳወቁ ማወቁ