Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊብዙ የተነገረለት የስንዴ ምርት እምን ላይ ይገኛል?

ብዙ የተነገረለት የስንዴ ምርት እምን ላይ ይገኛል?

ቀን:

በአበበ ፍቅር

ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገሮች መካከል በስንዴ ምርቷ በቀዳሚነት የምትታወቀው ኢትዮጵያ፣ በዓመት ከ107 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ፍላጎትን ትሻለች፡፡

ይህንን ፍላጎት ለማሟላት 17 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ከውጭ ስታጓጉዝ መቆየቷ ይታወቃል፡፡ ለዚህ ደግሞ ከ700 ሚሊዮን ዶላር እስከ አንድ ቢሊዮን ዶላር ፈሰስ ታደርግ እንደነበር ከዚህ በፊት የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በበጋና በመኸር ከቆላ እስከ ደጋ በስፋት የእህል ማሳ ላይ ምርትን የሚያመርቱ አርሶ አደሮች እንዳሏት የሚነገርላት ኢትዮጵያ፣ አሁንም ከእጅ ወደ አፍ የተሻገረ ምርት አምርተው በበቂ ለገበያ ሲያቀርቡ አይስተዋልም፡፡ ለዚህ ደግሞ በዘርፉ በርካታ ምክንያቶች በዋቢነት ሲቀርቡ ይስተዋላል፡፡

ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ፣ ኋላቀር የአመራረት ዘዴ፣ በተለይ አሁን ላይ አርሶ አደሩን እየፈተነ ያለው የአፈር ማዳበሪያ እጥረት፣ ድርቅና የመሳሰሉት ችግሮች በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡

አርሶ አደሩ ከዕለት ፍጆታ አልፎ ወደ ገበያ ለሸማቹ ማኅበረሰብ በሚያቀርብበት ወቅትም በኢመደበኛ የገበያ ሰንሰለት በማለፉ፣ ተጠቃሚው በፈለገው ጊዜ ሳይሆን ሻጮች በፈለጉትና በተመቻቸው ጊዜ በማቅረብ የተረጋጋ ገበያ እንዳይኖር ሲያደርጉ መቆየታቸው ይነገራል፡፡ 

በዚህ መካከል አርሶ አደሩ የልፋቱን ተመጣጣኝ ዋጋ ሳያገኝ፣ ሸማቹም በዋጋው መናር ሲማረር የሚጠቀመው በመካከል ጣልቃ የሚገባው ደላላ እንደሆነ በስፋት ይስተዋላል፡፡

ኢትዮጵያ በምግብ እህል ራሷን መቻል አቅቷት ቢሊዮን ዶላር አውጥታ ከውጭ ከማስገባት በዘለለ፣ ለዕርዳታ የብዙዎችን በር ስታንኳኳም ሰንብታለች፡፡

ኋላ ቀር የአስተራረስና የአመራረት ዘዴን ለበርካታ ዓመታት ስትከተል የኖረችው ኢትዮጵያ፣ የስንዴ ልመናን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ታሪክ ለማድረግ፣ የዜጎችን የስንዴ ፍላጎት ለማሟላትና ከፍጆታ የተረፉትን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በማቀድ ላለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት መጠነ ሰፊ የስንዴ ምርት ልማት ውስጥ ገብታለች፡፡ በተለይም በ2014 እና በ2015 ዓ.ም. የምርት ዘመን ከኢትዮጵያ ተሻግሮ ጎረቤት አገርን መመገብ የሚያስችል ይሆናል ተብሎ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው የስንዴ ምርትን ማልማቷና እያለማች መሆኗ በየመድረኩ ተነግሯል፡፡

ግምቱም ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ከዘርፉ ባለሙያዎችም አልፎ በአሜሪካ የውጭ ግብርና ቢሮም ‹‹በኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ትልቅ እመርታ እያሳየና ምርታማነቱ እየጨመረ ነው፤›› ተብሏል፡፡

በሪፖርቱ ላይም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. 2022 እና 2023 ውስጥ 5.7 ሚሊዮን ቶን ስንዴን ታመርታለች ብሎ ተንብዮ ነበር፡፡ ይህም ካለፈው የምርት ዘመን በ3.6 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑን አሳይቷል፡፡ 

ኢትዮጵያ የዜጎቿን አማካይ የስንዴ ፍላጎት ደረጃን በማሥላት ከዓመታዊ አማካይ የስንዴ ፍጆታ በላይ የሆነውን ለውጭ አገር ገዥዎች አቀርባሁ ካለች ወዲህ፣ ስንዴን ወደ ውጭ አገር መላክ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የስንዴ ላኪ ባለሀብቶች ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

በዚህም ባለሀብቶች ወደ ውጭ አገር የሚልኩት ስንዴ ከአገር ውስጥ ፍጆታ የተረፈውን እንደሆነ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ ተናግረው ነበር፡፡

መንግሥት ከዓምናው እጅጉን በላቀ ሁኔታ ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ትኩረት በመስጠት፣ ‹‹አንድም መሬት ፆም ማደር የለበትም!›› በማለት አርሶ አደሩን በክላስተር ወይም በኩታ ገጠም እንዲያርስ በማድረግ ከደጋ እስከ ቆላ፣ ከበጋ እስከ መኸር እየተሠራ እንደነበር የግብርና ሚኒስቴር ሪፖርት ያመለክታል፡፡

ዓምናና ዘንድሮ 2.8 ሚሊዮን ሔክታር በስንዴ ማሳ የተሸፈነ ሲሆን፣ ከእነዚህም ከ108 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡ ይህ አኃዝ በበጋ ወቅት ይመረታል ተብሎ የታሰበ 50 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴን ሳይጨምር እንደሆነ ተመልክቶ ነበር፡፡

ዘንድሮ በበጋ መስኖ ከአሥር ሚሊዮን ኩንታል የዘለለ ከዓመታዊ ፍጆታ በላይ ምርት እንደሚገኝ ግብርና ሚኒስቴር ቀደም ሲል ለሪፖርተር ገልጾ ነበር፡፡

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ጎተራ ሞልቶ የተረፈውን ለውጭ ገበያ አቅርባለሁ ስትል፣ ዘገባው በጣም የተጋነነና ከሁኔታዎች ጋር ያልተገናዘበ ነው በማለት የኢኮኖሚ ባለሙያዎች አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር፡፡ ከዚህም አንፃር የኢትዮጵያ የምግብ እጥረት ችግር የማይፈታ ነው ብለው ሞግተው ነበር፡፡

ነገሩ የፖለቲካ ፍጆታ ሳይሆን፣ የምግብ ፍጆታ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነው የሚሉ ሙያዊ አስተያየቶችም ተስተናግደው ነበር፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ በኩታ ገጠም በማረስ ስንዴን በበጋና በመኸር በገፍ የማምረት ሥራ ዳቦ በልቶ የማደር ጉዳይ ነው በማለት ሐሳባቸውን ያጋሩ ባለሙያዎችም ነበሩ፡፡

የ2014 ዓ.ም. የበጋና የመኸር ወቅት ተጠናቅቆ፣ የዘንድሮ የመኸር ምርት ማጠናቀቂያ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ ብዙ ከተዘመረለት የስንዴ ምርት ላይ ተቋዳሽ እንዳልሆኑ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡

ሕግና መመርያን ተከትለው፣ ምርትን ከአርሶ አደሩ ተረክበው፣ ለተጠቃሚው ኅብረተሰብ፣ እንዲሁም ለፋብሪካዎች የሚያቀርቡ ነጋዴዎችም የስንዴ ምርት በገበያው ላይ ለማግኘት መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡

ከአገር ፍጆታ ተርፎ ጎረቤት አገርን ይመግባል የተባለለት የስንዴ ምርት ወዴት ገባ? ሲሉ የሚጠይቁ ዜጎችም አልጠፉም፡፡ ነገሩ ፖለቲካን ሳይነካ ዳቦ በልቶ የማደር ጉዳይ ነው ከተባለ፣ ‹‹ዳቦ ወዴት አለ›› ሲሉ የሚጠይቁም አሉ፡፡ ጥያቄውን እንዲያነሱ ያደረጋቸው ደግሞ ከሰሞኑ በስንዴ፣ በዱቄትና በዳቦ ላይ እየታየ ያለው የዋጋ ጭማሪ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ 

የዱቄት ፋብሪካዎች የስንዴ እጥረት ገጥሞናል በማለት ለዳቦ ጋጋሪዎችና አከፋፋዮች ተናግረው፣ ተመጣጣኝ ያሉትን ዋጋ እንደጨመሩባቸው ሪፖርተር የቃኛቸው የዳቦ ቤት ባለቤቶች ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...