Thursday, March 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለሥራ አስፈጻሚዎች የከፍተኛ ደረጃ የቢዝነስ ትምህርት መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

ለሥራ አስፈጻሚዎች የከፍተኛ ደረጃ የቢዝነስ ትምህርት መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

ቀን:

በአበበ  ፍቅር

በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚሠሩ የሥራ አስፈጻሚዎች የከፍተኛ ደረጃ የቢዝነስ ትምህርት ሥልጠና የሚሰጥበት መርሐ ግብር ይፋ ሆነ፡፡

መርሐ ግብሩን በጋራ ይፋ ያደረጉት መቀመጫውን በኬንያ ያደረገው የስትራትሞር ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ትምህርት ቤትና በአዲስ አበባ የሚገኘው የካፒታል ቢዝነስ ትምህርት ቤት ናቸው፡፡

በ2014 ዓ.ም. ላይ የትብብር ስምምነት ያደረጉት ሁለቱ ተቋማት፣ የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የካዛና ግሩፕ ሊቀመንበርና የካፒታል ቢዝነስ ትምህርት ቤት ተባባሪ መሥራች አቶ አዲስ ዓለማየሁ እንደተናገሩት፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ደረጃ የትምህርት አሰጣጥ አጋርነትን ከልዩ ልዩ የትምህርት ተቋማት ጋር የአካዴሚክ ትብብር መሥራት ትልቅ ሀብት ነው፡፡

ይህም የሀብት አቅምና የልምድ መጋራትን ስለሚፈጥር የጎለበተ የሥልጠና አቅርቦት ለመስጠት አመቺ ይሆናል ሲሉም አክለዋል፡፡

የስትራትሞር ቢዝነስ ትምህርት ቤት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሲዛር ምዋንጊ በበኩላቸው፣ ሁለቱ አጋር ድርጅቶች እርስ በርስ በመደገፍ ለጠንካራ የትምህርት አሰጣጥና የላቀ የአፈጻጸም ባለሙያ ለማፍራት ዕርምጃ ጀምረዋል ብለዋል፡፡

ሌላው በመክፈቻው ላይ የተገኙት የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ግሎባል ሊቀመንበር አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ባደረጉት ንግግር፣ የንግድ ልማት ትምህርት መጪው ትውልድ እምቅ የሆነውን የአገር ሀብት በር የሚከፍትበት ወሳኝ መንገድ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በማደግ ላይ ባሉ ኢኮኖሚዎችና በካፒታል ገበያው ላይ ጥልቅ ግንዛቤ ያለው፣ ለመልካም አስተዳደር ቁርጠኛ የሆነና ለአገር ጠቃሚ የሆኑ የኢንቨስትመንት ውሳኔዎችን የሚወሰን ጠንካራ አመራር የሚፈጠርበትን ትውልድ ማፍራት የዚህ ትምህርት ተቋም ዋና ግብ ይሆናል ብለዋል፡፡

ስትራትሞር ቢዝነስ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ውስጥ ባሉ በመንግሥትና በግል ሴክተሮች ላይ በሚሰማሩ የሥራ አስፈጻሚዎችና አመራሮች ላይ ተፅዕኖ የማድረግ ኃላፊነት ከወሰዱት ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንዱ ነው ያሉት ሲዛር ምዋንጊ (ዶ/ር)፣ ከንግድ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፕሮጀክቶች፣ ጥናቶች፣ የተመረጡ ዓለም አቀፍ ትብብሮችንና ሽርክናዎችን በመጠቀም፣ በቂ ዓለም አቀፋዊ የሥራ አስፈጻሚና የንግድ አስተዳደር እንዲሁም የአመራር ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ኅብረተሰቡ ለይ ለውጥ ለመፍጠር የሚሠራ ተቋም መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በቢዝነስ ማኔጅመንትና በሥራ አመራር ላይ በማተኮር ጠንካራ የሆኑ ዓለም አቀፍ የሥራ አስፈጻሚ ፕሮግራሞችን በመንደፍ የሥራና የንግድ አስፈጻሚ ትምህርትን በድኅረ ምረቃና በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች አዳዲስ ዕውቀቶችን ለሠልጣኞች ለማስታጠቅ ድንበሩን አስፍቶ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው ሲሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አብራርተዋል፡፡

ከኢትዮጵያው ካፒታል ቢዝነስ ትምህርት ቤት ጋር በጋራ ለመሥራት መወሰኑና መጣመሩ ከዕርምጃዎቹ አንዱ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

የካፒታል ቢዝነስ ትምህርት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አዲስ ዓለማየሁ በበኩላቸው ድርጅታቸው እ.ኤ.አ. በ2022 በካዛና ግሩፕ ሥር መመዝገቡን አንስተው በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ ላይ ልዩ የአስፈጻሚ ትምህርት ለመስጠት የተቋቋመ ድርጅት ነው ብለዋል፡፡

ኮርሶቹም በተለያዩ ደረጃዎች ላይ ለሚገኙ ድርጅቶች እንዲስማሙ ተደርገው የተዘጋጁ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...