Saturday, April 20, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ስለፖለቲካ ማርኬት ፕሌስ ጽንሰ ሐሳብ አጥንተው ከፍተኛ አመራሮችን ሲያሠለጥኑ ቢሰነብቱም ዛሬ ከባለቤታቸው የተነሳውን ጥያቄ ለመመለስ ተቸግረዋል]

 • እኔ ምልህ ክቡር ሚኒስትር?
 • ክቡር ሚኒስትር ካልሽኝ ችግር አለ ማለት ነው።
 • ችግርማ አለ።
 • እሺ … እኔ ምልህ ያልሽው ለምን ነበር?
 • ልጠይቅህ ነዋ።
 • ምን?
 • ከጥቂት ሳምንታት በፊት ስትሰብኩት የነበረው ነገር የውሸት ነው ማለት ነው?
 • ምን ሰበክን?
 • በመጀመሪያ የፓርቲ አባሎቻችሁን ቀጥሎ ማኅበረሰቡን ስለፖለቲካ ማርኬት ፕሌስ ወይም ስለፖለቲካ ገበያ ስትግቱ አልነበረም እንዴ?
 • አዎ፣ ስለአገሪቱ የፖለቲካ ገበያ መበላሸት ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ አሁንም እየሠራን ነው።
 • ግን እናንተ ራሳችሁ ስለጽንሰ ሐሳቡ ግንዛቤ አላችሁ?
 • እንዴት? ምን ዓይነት ጥያቄ ነው?
 • መንግሥት ራሱ የፖለቲካ ሸቀጥ ይዞ ገበያ መውጣቱን ስመለከት ጊዜ ግራ ገብቶኝ ነዋ፡፡
 • መንግሥት እንዴት እንደዚህ ያደርጋል? ጽንሰ ሐሳቡ አልገባሽም ማለት ነው?
 • የፖለቲካ ገበያ ማለት የፖለቲካ ሥልጣን ለመያዝ ወይም የመንግሥትን ሥልጣን ለማፅናት ለገበያ የሚያቀርብ ሸቀጥ አይደለም እንዴ?
 • ትክክል ነሽ፣ አንዱ መገለጫው እሱ ነው።
 • ሥልጣንን ለማፅናት የብሔር ወይም የሃይማኖት ድጋፍ ለማግኘት መትጋት የፖለቲካ ሸቀጥ አይደለም?
 • ነው እንጂ፣ እንዲያውም አደገኛው እሱ ነው።
 • የፖለቲካ ገበያው መበላሸት የሚያስከትለው ውጤት ተቋምን፣ ቀጥሎም አገርን የማፍረስ አደጋ ያስከትላል ስትሉም ሰምቻለሁ አይደል?
 • ትክልል ነሽ? ይህ አዝማሚያ አደገኛ ነው ያልንበት ምክንያት አገር ስለሚያፈርስ ነው።
 • ታዲያ አገር በሆነችው ቤተ ክርስቲያን ላይ ለምን መዝመት ፈለጋችሁ?
 • እሱ እንኳን ከዚህ ጋር አይገናኝም።
 • እንዴት አይገናኝም?
 • የሃይማኖት ጉዳይ ስለሆነ።
 • የሃይማኖት ጉዳይ ብቻ እንዳልሆነማ ግልጽ ነው።
 • እንዴት?
 • ነገሩ የሲኖዶሱን አብላጫ ለመቆጣጠር ወይም አገር ናት ያላችኋትን ተቋም ለመከፋፈል የሚደረግ ጥረት ነው።
 • ለምን ብለን እንደዚያ እናደርጋለን?
 • ለማፅናት ፈልጋችሁ ይመስለኛል።
 • ምን ለማፅናት?
 • ሥልጣናችሁን፡፡
 • በፍፁም፣ ተሳስተሻል፡፡
 • ታዲያ ለምን ችግሩን ለመፍታት ሰነፋችሁ?
 • ሰንፈን አይደለም።
 • እና ምን ሆናችሁ ነው?
 • መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት ስለማይችል ነው።
 • ታዲያ ለምን እናንተ ገባችሁ?
 • አልገባንም?
 • የቤተ ክርስቲያን ተቋማትን እየሰበሩ መቆጣጠር የጀመሩትን እያያችሁ ዝም ማለታችሁ እኮ ያው ነው።
 • ያው ነው ማለት?
 • ጣልቃ መግባት ነው፡፡
 • በፍፁም! የመንግሥት ፍላጎት ራሳቸው ተነጋግረው ልዩነታቸውን እንዲፈቱት ብቻ ነው።
 • የአዲስ አበባ ባለአደራ አስተዳደር በሚል ተጀምሮ የነበረውን እንቅስቃሴ ታስታውሳለህ?
 • አዎ፣ እሱን በምን አስታወሽው?
 • በወቅቱ የነበረው ጭንቀታችሁ ትዝ ብሎኝ ነው።
 • በአንድ ከተማ ላይ ሁለት አስዳደር ለመፍጠር መሞከር ትክልል አይደለም፣ በዚያ ላይ አካሄዱ አስፈሪ ነበር።
 • ቢሆንም ከማሰር ይልቅ በውይይት ብትፈቱት ይሻል ነበር።
 • እንዴት አድርገን ነው ከእነሱ ጋር የምንወያየው?
 • አሁን የቤተ ክርስቲያን ችግር በውይይት ይፈታል እንዳልከው።
 • እሱ ሌላ! ያ ሌላ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...

እጥረትና ውጥረት!

ጉዞ ከስድስት ኪሎ ወደ ቃሊቲ፡፡ ‹‹ይገርማል ቀኑ እንዴት ይሄዳል?››...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪው ቅሬታ የቀረበባቸው አንዳንድ ጉዳዮችን ክቡር ሚኒስትሩ ተመልክተው ምላሽና ውሳኔ እንዲሰጡባቸው ለማድረግ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር እየተወያዩ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር ተቋማችን በሚሰጣቸው አንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ጥያቄ እየተነሳ በመሆኑ ነው ዛሬ ከእርስዎ ጋር ለመወያየት የፈለግኩት። የምን ጥያቄ? ማነው ጥያቄውን ያቀረበው? ጥያቄውን ያቀረቡት የተቋማችን ተገልጋዮች ናቸው። እሺ፣...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

እኔ እምልህ ...ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ? ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው? ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!? አልገባኝም? አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት? አዎ። ኤል...