Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልበመልካ ቁንጥሬ 1.2 ሚሊዮን ዓመታትን ያስቆጠሩ የድንጋይ መሣርያዎች ተገኙ

በመልካ ቁንጥሬ 1.2 ሚሊዮን ዓመታትን ያስቆጠሩ የድንጋይ መሣርያዎች ተገኙ

ቀን:

በኢትዮጵያ አዋሽ ሸለቆ ላይ 1.2 ሚሊዮን ዓመታትን ያስቆጠሩ የድንጋይ መሣሪያዎችን ማግኘቱን በስፔን ከሚገኙ የምርምር ተቋማት ጋር የተቆራኘው የተመራማሪዎች ቡድን አስታውቋል፡፡ኮስሞስ ማጋዚን፣ የምርምር ቡድኑ ግኝቱን ያሳተመበትን ኔቸር ኢኮሎጂና ኢቮሉሽን ጆርናል ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በመልካ ቁንጥሬ የአርኪዮሎጂ መካነ ቅርስ የተገኙት የድንጋይ መሣሪያዎች 578 ናቸው፡፡ቅድመ ሰው ለልዩ ልዩ አገልግሎት ይጠቀምባቸው የነበሩት ድንጋዮች (ባልጩት) የተገኙበት አካባቢ በወርክሾፕነት ያገለገለ መሆኑም ተገልጿል፡፡እነዚህ 1.2 ሚሊዮን ዓመታት የቆዩና በቁፋሮ የተገኙት ባልጩት መሰል ድንጋዮች በቅድመ ታሪክ የድንጋይ ጠረባ ወርክሾፕ (Knapping Workshop) እንደነበሩ የሚያሳዩ ናቸው ብሏል የጥናት ቡድኑ፡፡ መጥረብ (ጠረባ) የእጅ ሥራን ለመፍጠር የሚያገለግል ‹‹የመጀመሪያው ታላቅ ፈጠራ›› ተብሎ ይታሰባል፡፡ ከዚህ ቀደም በተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ የድንጋይ ጠረባ ወርክሾፕ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ በቅድመ ታሪክ የተመዘገበው ከ774 ሺሕ ዓመታት እልፍ ያላለ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ግኝት ግን ቀደም ሲል ከተገመተው በእጥፍ ሊጨምር ይችላል፡፡ተመራማሪዎቹ በመልካ ቁንጥሬ መካነ ቅርስ 578ቱን የድንጋይ መሣሪያዎች ያገኙት በደለል ውስጥ ተቀብረው ነው፡፡ በዙሪያቸው ያሉትን ነገሮች በመተንተን የመሣሪያዎቹን ዕድሜ 1.2 ሚሊዮን እንደሆነ ለመገመት አስችሏቸዋል፡፡መጥረቢያዎቹን ሲመረምሯቸው አገነባባቸው ተመሳሳይ መሆኑም ተመልክቷል፡፡ የትኞቹ የቅድመ ሰው ዝርያዎች (ሆሚኒዎች) መሣሪያዎቹን እንዳመረቱ በትክክል አልታወቀም ያለው ሰነዱ፣ ሊሆን የሚችለው ከሁለት ሚሊዮን ዓመታት በፊት በአፍሪካ ውስጥ ብቅ ያለውና ከ100 ሺሕ ዓመታት በፊት ከቅሪተ አካላት መዝገብ የጠፋው ሆሞ ኢሬክተስ ይመስላል ብሏል፡፡ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው መልካ ቁንጥሬ በ2,000 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ፣ በኢትዮጵያ አምባ ላይ የተዘረጋ የአርኪዮሎጂ ቦታ ሲሆን፣ ከሁለት ሚሊዮን እስከ አምስት ሺሕ ዓመታት በፊት ድረስ ያለውን እጅግ በጣም ብዙ የሆነ የአርኪዮሎጂ ቅሪት የያዘ ነው፡፡ በታንዛኒያ ካለው ኦልዱቫይ ሸለቆ ጋር የሚነፃፀር ቢሆንም መልካ ቁንጥሬ ግን ከሳቫና አካባቢ በግልጽ የሚለየው በቀዝቃዛና ዝናባማ የአየር ጠባይ ብቻ ሳይሆን፣ ልዩ በሆኑ ዕፀዋትና እንስሳት ዝርያዎቹም ነው።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ2.6 ሚሊዮን ዓመታት ወዲህ ባለው ጊዜ ውስጥ የቅድመ ሰው ዘር አውራሾች በየዘመኑ የተለያዩ ዓይነት የድንጋይ መሣሪዎችን ይጠቀሙ ነበር፡፡ በተለይም ከ1.75 ሚሊዮን ዓመታት ጀምሮ እስከ 200 ሺሕ ዓመታት ድረስ በነበረው 1.5 ሚሊዮን ዓመታት ጊዜ ውስጥ ‹‹አሹሊያን›› በመባል የሚታወቁ በሁለት ገጽ የተጠረቡ የድንጋይ መሣሪዎች ተሠርተው አገልግሎት ላይ የዋሉ ሲሆን፣ እነዚህን የእጅ መዳፍ ቅርፅ ያላቸው የድንጋይ መሣሪያዎች የሠራቸው ሆሞ ኢረክተስ (Homo erectus) በመባል የሚታወቀው ጥንታዊ የቅድመ ሰው ዘር ነው፡፡ ይህ ዝርያ በኮንሶ መካነ ቅርስ ከ1.75 ሚሊዮን እስከ 800 ሺሕ ዓመታት በነበሩት ዘመናት ውስጥ ይኖር እንደነበረ መረጋገጡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በዚህም ጊዜ ውስጥ አሹሊያን ተብለው ከሚጠሩ የድንጋይ መሣሪዎች በተጨማሪም ከ1.4 ሚሊዮን ዓመታት በፊት የጉማሬ የታፋ አጥንት (femur) በመጠቀም ተመሳሳይ የመቁረጫ መሣሪያ ሠርተው መጠቀማቸውን ከዓመታት በፊት በኮንሶ መካነ ቅርስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...