Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅግመሎቹና ሰውዬው

ግመሎቹና ሰውዬው

ቀን:

በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። ታዲያ ይህ ሰው፣ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በኑሮው ከሚገጥመው ችግር የተነሳ፣ ሁልጊዜም በሕይወቱ ደስተኛ አልነበረም፡፡ አንድ ቀን ግን ከሚኖርበት ሥፍራ በቅርብ ርቀት የምትገኝ ከተማ ዘንድ፣ አንድ ታላቅ የሃይማኖት አባት ከአጃቢዎቻቸው ጋር እንደመጡ ይሰማል። ይህን ጊዜም እኚህን አባት ማግኘት አለብኝ ብሎ ይወስናል።

በመሸም ጊዜ እኚህ አባት ያሉበት ሥፍራ ይደርስና እሳቸውን ለማግኘት ቁጭ ብሎ መጠባበቁን ይይዛል። ከረዥም ቆይታ በኋላም እኒያን አባት ያገኝና ጥያቄውን ይጀምራል። ‹‹አባቴ ሆይ በሕይወቴ ፍፁም ደስተኛ አይደለሁም፡፡ በቃ ሁሌም በችግር የተከበብኩኝ ሰው ነኝ… በዚህ በኩል የሥራ ጭንቀት፣ በዚህ ደግሞ የጤና ቀውስ፣ በዚያ ላይ የቤቴ ውስጥ ችግር… ብቻ ተደማምሮ ዕረፍት ነስቶኛል፣ ደስታም ርቆኛል፡፡ እባክዎትን አንዳች የመፍትሔ ሐሳብ ይስጡኝና፡ ደስተኛና የሰላም ኑሮ እንድኖር ይርዱኝ!››

ሽማግሌውም ፈገግ ብለው ‹‹ልጄ ለችግርህ ነገ ጠዋት ላይ መፍትሔ እሰጥሃለሁ፡፡ ነገር ግን አሁን ባዝህ፣ ጥቂት የኔን ሥራ ልትሠራልኝ ትችላለህን? ሰውዬውም በዚህ ይስማማል። እሳቸውም ቀጥለው ‹‹በጉዞአችን የያዝናቸው መቶ ግመሎች በዚህ ይገኛሉ፡፡ እናም ዛሬ ምሽት የእነሱን ነገር አደራውን ላንተ ሰጥቻለሁ፡፡ ሁሉንም ግመሎች መሬት ላይ ካስቀመጥክ በኋላ ወደ መኝታ መሄድ ትችላለህ፤›› ይህንንም ብለው ወደ ድንኳናቸው ሲያቀኑ፣ ሰውዬውም የታዘዘውን ሊያደርግ ምሽቱን ግመሎቹ ዘንድ አመራ።

በቀጣይ ቀንም ሽማግሌው ማልደው ወደ ሰውዬው በማቅናት ‹‹ልጄ ሌሊቱን ጥሩ ተኝተህ አደርክ?›› ብለው ይጠይቁታል። ሰውዬው ግን ሐዘን በተሞላበት ስሜት ሆኖ ‹‹አባቴ ለአፍታ እንኳን እንቅልፍ ሳይወስደኝ ነው ሌሊቱ የነጋው። ብዙ ለፋሁ፣ ብዙም ጣርኩኝ ይሁንና በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች እንዲቀመጡ ማድረግ አልቻልኩም፡፡ አንዳንዶቹ ራሳቸው ይቀመጣሉ፡፡ አንዳንዶቹ ግን ላስቀምጣቸው ብሞክርም እንኳን አይቀመጡም፡፡ አንዱ በዚህ በኩል ሲቀመጥ በሌላ በኩል ያሉት ይነሳሉ፤››

ይህን ጊዜ ሽማግሌው ፈገግ እያሉ እንዲህ አሉ ‹‹ካልተሳሳትኩኝ ይህ የሆነው ትላንት ማታ ነው አይደል?››

– ራሳቸውን በራሳቸው ያስቀመጡ ብዙ ግመሎች ነበሩ!?

– ብዙዎቹ ደግሞ በአንተ ጥረት ሊቀመጡ ችለዋል!?

– ቀሪዎቹ ልታስቀምጣቸው ሞክረህ እንኳን አልተቀመጡም ከቆይታ በኋላ ግን በጊዜ ውስጥ ራሳቸውን አስቀምጠው አግኝተሃቸዋል!?

ሰውዬውም ‹‹አዎ! አዎ!…ትክክል!›› ብሎ መለሰ።

ሽማግሌውም ቀጠሉና ‹‹ስለዚህ አሁን አንድ ነገር ተረዳህን? በሕይወት ያሉም ችግሮች እንዲሁ ናቸው…

– አንዳንዶቹ በራሳቸው መፍትሔ ያገኛሉ።

– አንዳንዶቹ በአንተ ጥረት መፍትሔ ያገኛሉ።

– አንዳንዶቹ ደግሞ በአንተ ጥረት እንኳን አይፈቱም፡፡ እነዚህን ችግሮች ለጊዜ ተዋቸው። ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ በራሳቸው ይፈታሉና/መፍትሔ ያገኛሉና።

ትላንት ማታ፣ ምን ያህል ብትሞክር በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች ማስቀመጥ እንዳልቻልክ ትምህርት ወስደሃል። አንዱን ግመል በዚህ ጋር ስታስቀምጥ በሌላ በኩል ያሉት ይነሳሉ። ልክ እንዲሁ እዚህ ጋር አንዱን ችግር ፈታሁ/ተፈታ ስትል እዚያ ደግሞ ሌላ ችግር ተነስቶ ይጠብቅሃል። ሕይወት እንዲህ ነውና። ችግሮች የሕይወት አካል ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ጥቂት ሌላ ጊዜ ደግሞ በርካታ ችግሮች ይኖራሉ። ይሄ ማለት ግን ስለነሱ ሁሌ ማሰብ አለብህ ማለት አይደለም። እነሱን ለጊዜ እየተወክ ወደፊት ተጓዝ። በእያንዳንዱ ዕርምጃም ወደ ዓላማ ሕይወት፡፡ ማደ

  • ሙቫ አማን በቡክ ፎር ኦል
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...