Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለካንሰር ታማሚ ሕፃናት የተደረገ ድጋፍ

ለካንሰር ታማሚ ሕፃናት የተደረገ ድጋፍ

ቀን:

በኢትዮጵያ በካንሰር በሽታ ተይዘው የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት ችግር ውስጥ የወደቁ ሕፃናትን ለመታደግ እየሠራ የሚገኘው ተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ካንሰር ድርጅት (ታፕኮ) ከዳላስ ቴክሳስ ነዋሪዎችና ከአርሰናል ደጋፊዎች 1,810,786.00 ብር ድጋፍ አግኝቷል፡፡

ከዳላስ ቴክሳስ ነዋሪዎችና ከአርሰናል ደጋፊዎች ተሰብስቦ የተገኘውን ብር ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ለተቋሙ የተበረከተ ሲሆን፣ ድጋፉም በካንሰር በሽታ ተይዘው በገንዘብ ምክንያት የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ለማይችሉ ሕፃናት እንደሚውል ተገልጿል፡፡

የታፕኮ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳራ ኢብራሂም እንደገለጹት፣ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ለካንሰር በሽታ የተጋለጡ ሕፃናትን ለመታደግ የተደረገው ድጋፍ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

ተቋሙ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅት ሆኖ፣ በፌዴራል መሥሪያ ቤቱ ሕግና ደንብ መሠረት በአዋጅ ቁጥር 621/2009 መሠረት ተቋቁሞ መሥራት ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ከ2,000 በላይ ታካሚዎች ሕክምናቸው እንዳይቋረጥ ከማደሪያ አንስቶ እስከ ምግብ፣ መድኃኒት፣ ትራንስፖርት፣ የሥነ ልቦና ምክርና ሌሎች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አብዛኛውን ጊዜ በዚህ ችግር ውስጥ የሚገኙ ሕሙማን ተገቢውን የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ተቋሙ ሁኔታዎችን እያመቻቸ ቢሆንም፣ አልፎ አልፎ የመድኃኒት እጥረት እየገጠመው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በቀን 50 የሚሆኑ ሕፃናት ልጆች በማዕከሉ እየገቡ የተለያዩ አገልግሎቶች እያገኙ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ ሳራ፣ ድርጅቱም በዋናነት የሕፃናት ካንሰርን ለመከላከልና የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት አልሞ የሚንቀሳቀስ መሆኑን፣ ይህንንም ተፈጻሚ ለማድረግ ከጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል፣ ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፣ ከጅማ ዩኒቨርሲቲና ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ጋር በመሆን እየሠራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

የሕክምና አገልግሎቱን የሚያገኙ የካንሰር በሽታ ሕሙማን ዕድሜያቸው ከአንድ እስከ 15 ዓመት ክልል ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት ብቻ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ አገልግሎቱን ሲያገኙ አስታማሚ ወላጆቻቸው የማደሪያና የሌሎችም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ተዘፍቀው የሚገኙ ዜጎችን ለመርዳት የዳላስ ቴክሳስ ነዋሪዎችና የአርሰናል ደጋፊዎች ከዚህ በፊት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን፣ የዳላስ ነዋሪው አቶ በፈቃዱ ግርማ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የዳላስ ነዋሪዎችም ሆኑ የአርሰናል ደጋፊዎች እንዲህ ዓይነት ድጋፎች በመሰብሰብ ለተቸገሩ ወገኖች መስጠት ከጀመሩ አምስት ዓመታት እንደሆናቸውና ከዚህ በፊትም እንዲህ ዓይነት ድጋፍ ለመቄዶንያ መሰጠቱን አቶ ፈቃዱ አክለው ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም በተለያየ ምክንያት ወደ ጎዳና የወጡ ዜጎችን ለመደገፍ ዕቅድ መያዛቸውን፣ ይህንንም ተፈጻሚ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...