የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)፣ በ83ኛው የአገው ፈረሰኞች ማኅበር የምሥረታ በዓል ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዊ ዞን እንጅባራ ከተማ ሲከበር የተናገሩት፡፡ አያይዘውም ከአገው ፈረሰኞች ጽናትን እንማራለን፣ ለ83 ዓመታት ያለመቋረጥ የተከበረው በዓል ጽናትን ያስተምራል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ለዓመታት በዓሉን በማክበር፣ ፈረሰኞች የሠሩትን ገድል በማስታወስና የፈረስን ጥቅም በማሳየት የባህል መገለጫ አድርገው ይዘውት ቀጥለዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በዓሉ ቱሪስት እንዲስብ፣ ሀብት እንዲያመጣና የሥራ ዕድል እንዲፈጥር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡