የአገው ፈረሰኞች ማኅበር 83ኛው የምሥረታ ክብረ በዓል፣ ‹‹አምራች ዘማች የአገው ፈረሰኞች ማኅበር›› በሚል መሪ ቃል ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በእንጅባራ ከተማ ተከብሯል፡፡ ማኅበሩ የፋሺስት ጣሊያን ወረራ ተከትሎ በ1932 ዓ.ም. ከ30 በማይበልጡ አባላት የተመሰረተ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከ60 ሺሕ በላይ አባላት እንዳሉት ይነገራል፡፡ ክብረ በዓሉ ካሉት ትውፊቶች አኳያ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን በብሔራዊ ቅርስነት የተመዘገበ ሲሆን በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች ለማስመዝገብ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው ተብሏል፡፡ ፎቶዎቹ የክብረ በዓሉን ገጽታ በከፊል ያሳያሉ፡፡
- ፎቶ ከማኅበራዊ ገጽ