Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአማራ ክልል በሀብት ምዝበራ ወንጀል ላይ ማስረጃ ከጠፋ በድርድር ለማስመለስ የሚያስችል መመርያ...

የአማራ ክልል በሀብት ምዝበራ ወንጀል ላይ ማስረጃ ከጠፋ በድርድር ለማስመለስ የሚያስችል መመርያ አወጣ

ቀን:

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የተመዘበረን ሀብት በወንጀል ከሶ ለማስመለስ በቂ ማስረጃ ሳይኖር ሲቀር፣ ‹‹ለሕዝብ ጥቅም ሲባል›› በሚል ሀብቱን በድርድር ለማስመለስ የሚያስችል መመርያ አወጣ፡፡

በወንጀል የተገኘ ሀብትን ምርመራ የሚያካሂድበትና የማስመለስ ሥራ የሚያከናውንበት መመርያና ማኑዋል በክልሉ የፍትሕ ቢሮ በተፈረመ ደብዳቤ፣ ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ለክልልና ለዞን ፍትሕ ቢሮዎች መላኩን ሪፖርተር ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በመመርያ ተደግፎ በወጣው የሥራ ማኑዋል (መመሪያ) በወንጀል ድርጊት የተመዘበረን ሀብት በድርድር ማስመለስ የሚቻለው፣ በዋናው ምርመራ ላይ ወንጀሉን በሚገባ ለማስረዳት የሚያስችል ማስረጃ ስላለመኖሩ በሚመለከተው የሥራ ክፍል በጽሑፍ ሲረጋገጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ድርድር የሚካሄደውም ወንጀሉን ለማስረዳት የሚያስችል በቂ ማስረጃ ቢኖርም፣ ከተፈጸመው ምንዝበራ አንፃር ተመጣጣኝ ሀብት ተፈልጎ ያልተገኘ ሲሆን፣ ወይም ‹‹ለሕዝብ ጥቅም›› በሚል የወንጀል ክሱ ሲቋረጥና ተከሳሽ የመዘበረውን ንብረት ሙሉ ለሙሉ ሲመልስ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የሥራ ማኑዋሉ ተከሳሹ ክሱ ከመነሳቱ በፊት ንብረቱን መመለስ የማይችልበት ሁኔታ ሲኖር፣ ለንብረቱ አመላለስ በበቂ ዋስትና የተደገፈ ዝርዝር የውል ስምምነት እንዲፈርም መደረግ እንዳለበት ያብራራል፡፡

ተከሳሹ በገባው ውል ስምምነት መሠረት ለመፈጸም ፈቃደኛ ካልሆነ፣ ውሉ እንዲፈጸም ዓቃቤ ሕግ የፍትሐ ብሔር ክስ እንደሚያቀርብ የሚያብራራው የሥራ ማኑዋሉ፣ በድርድር የሚመለሰው ንብረት በወንጀሉ ከደረሰው ጉዳት ወይም ያላግባብ ከተገኘው ጥቅም ጋር ተመጣጣኝ መሆን እንደሚገባው ያትታል፡፡

ተከሳሹ የመዘበረውንና ያልተገኘውን ንብረት ለመመለስ የክስ መቋረጥን እንደ ቅድመ ሁኔታ በሚያነሳበት ጊዜ የሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ኃላፊና የሚመለከተው የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ክሱ መቋረጥ ያለበት ስለመሆኑ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ እንዳለባቸው፣ ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ተከሳሹ ለሚመለከተው የተቋሙ የበላይ አመራር አቤቱታ ሊያቀርብ እንደሚችል ማንዋሉ ያስረዳል፡፡

ተከሳሹ ንብረቱን ለመመለስ የሚገባው የስምምነት ቃል ከሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ ጋር በጽሑፍ በሚደረግ ውል መረጋገጥ እንዳለበት የተገለጸ ሲሆን፣ ተከሳሹ ውሉን ከፈጸመ በኋላ ንብረቱን በሰጠው ቃል መሠረት ካልመለሰ የወንጀል ክሱ ከተቋረጠ በኋላ ከስድስት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መንቀሳቀስ እንደሚኖርበት ተመላክቷል፡፡

በክልሉ ፍትሕ ቢሮ ለሕዝብ ጥቅም ተብሎ የሚቋረጥ መዝገብ የሀብት ማስመለስ ጉዳይን የሚመለከት ከሆነ የተመዘበረው ሀብት ስለመመለሱ መረጋገጥ አለበት፡፡ ነገር ግን ይህ ሳይደረግ ቀርቶ መዝገቡ ከተቋረጠ የወንጀል ክሱ የተቋረጠለት ሰው፣ ይህንኑ ሀብት እንዲመልስ ክሱ እንዲቋረጥ ትዕዛዝ በሰጠው ኃላፊ በጽሑፍ ወይም በማናቸውም ሕጋዊ መንገድ ሊገለጽለት እንደሚገባና የሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ ይህንን ጉዳይ ተከታትሎ ማስፈጸም እንዳለበት ተብራርቷል፡፡

በወንጀል ምርመራ፣ ክስ አቀራረብ ወይም ክርክር ሒደት ወደ ምስክርነት እንዲዞር የተደረገ ተጠርጣሪ ወይም ተከሳሽ፣ በወንጀል ድርጊቱ ያገኘውን ያልተገባ ጥቅም መመለሱ መረጋገጥ እንደሚኖርበት የተገለጸ ሲሆን፣ የተመዘበረ ንብረት በድርድር እንዲመለስ ስምምነት በተደረገ ጊዜ አስቀድሞ የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ የንብረት ማስመለሱ ውል እስኪፈጸም ድረስ ፀንቶ መቆየት እንዳለበት በማንዋሉ ተጠቁሟል፡፡

ክልሉ ከፍትሕ መምርያዎች እስከ ወረዳ ጽሕፈት ቤቶች ድረስ የሥራ ክፍሎችን እንደ አዲስ በማደራጀት ወደ ሥራ መግባቱ በመመርያው ተገልጿል፡፡ በመመርያ ተደግፎ የወጣው ማንዋል በወንጀል የተገኘ ሀብትን የመመርመርና የማስመለስ ሥራ ውስጥ የሚሳተፉ ባለሙያዎችንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን የሥራ ድርሻ ለይቶ ለማስቀመጥ፣ ግልጽነት ያለው አሠራርና ተጠያቂነትን ለመዘርጋት፣ ሥራዎች ወጥነት ባለው አግባብ እንዲከናወኑ ለማስቻል የሚያግዝ መሆኑ ተብራርቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...