ከአራት ዓመታት በፊት በተከሰሱበት በከባድሙስና ወንጀል ስድስት ዓመታት ተፈርዶባቸው የነበሩት አቶ በረከት ስምፆን ዛሬ ጥር 17 ቀን 2015 ዓም ከእስር መፈታታቸውን ሪፖርተር ከቤተሰቦቻቸው አረጋግጧል።
በቀድሞ ስሙ ጥረት ኮርፖሬትን ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲመሩ ከዳሽን ቢራና ሌሎች ኩባንያዎች ጋር በተያያዘ ተፈፅሟል በተባለ ሙስና፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስድስት ዓመታት በእስር እንዲቀጡ መወሰኑ ይታወሳል። አቶ በረከት ከእስር የተፈቱት በአመክሮ ይሁን ወይም በሌላ ምክንያ ለማጣራት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ከአቶ በረከት ጋር ተከሰው ስምንት ዓመታት የተፈረደባቸው አቶ ታደሰ ካሳ በእስር ላይ ናቸው።