Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልታላቁ የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ዓለም አቀፍ የሥዕል ሲምፖዚየም ሊካሄድ ነው

ታላቁ የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ዓለም አቀፍ የሥዕል ሲምፖዚየም ሊካሄድ ነው

ቀን:

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ዓለም አቀፍ የሥዕል ሲምፖዚየም እንደሚካሄድ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

‹‹መነሻ›› በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውና ከጥር 18 እስከ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባና በባህር ዳር ከተማ የሚካሄደው የሥዕል ሲምፖዚየም ላይ፣ ከኢትዮጵያና ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ 25 ሠዓሊዎች ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡

 ጽሕፈት ቤቱ ከአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እንዲሁም ከኬታ የማስታወቂያና የሥዕል ስቱዲዮ ጋር በመሆን ሰኞ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የጽሕፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት የሚዲያ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም እንደገለጹት፣ ከዚህ በፊት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ሲደረግ በኪነ ጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ትልቅ ሚና መጫወታቸውንና ይህም የሥዕል ሲምፖዚየም የዚሁ ማሳያ ነው፡፡

በሥዕል ሲምፖዚየሙ ከዓባይ ተፋሰስና ከተለያዩ አገሮች 25  ሠዓሊያን እንደሚሳተፉና የዓባይ መፍለቂያ ወደ ሆነችው ሰከላ በማቅናትና ጉብኝት አድርገው ሥዕሎቻቸውን በተዘጋጁላቸው ጀልባዎች ላይ ሠርተው እንደሚያቀርቡ የሲምፖዚየሙ አዘጋጅ ሠዓሊ ታምራት ሡልጣን በመግለጫ ወቅቱ ተናግረዋል፡፡

ሠዓሊዎቹ በባህር ዳር ከተማም የነበራቸውን ቅኝት ከጨረሱ በኋላ በአዲስ አበባ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ሥራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ ይደረጋል ያሉት አዘጋጁ፣ የሲምፖዚየሙ ፅንሰ ሐሳብም ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት ማስተዋወቅና የዘርፉ ተዋናዮችን እርስ በእርስ ማስተሳሰር እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

በሥዕል ሲምፖዚየሙ የህዳሴውን ግድብ  በሥነ ጥበብ አማካይነት ለዓለም ማስተዋወቅ እንደሚቻል የተናገሩት የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የኪነ ጥበብ ዘርፍ ኃላፊው አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት ናቸው፡፡  እንደነዚህ ዓይነት የሥዕል ሲምፖዚየም መዘጋጀቱ ሥነ ጥበብ ያላትን አቅም በመጠቀም የዓባይ ወንዝ መነሻ ኢትዮጵያ መሆኗን ለማሳየት እንደሚረዳም ገልጸዋል፡፡

የተለያዩ አገሮች የሚሳተፉበት ይህ የታላቁ ህዳሴ ግድብ አስመልክቶ የተዘጋጀው የሥዕል ሲምፖዚየም ለሰባት ተከታታይ ቀናት በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚና የመዝጊያ ዝግጅቱ ጥር 27 ቀን በወዳጅነት ፓርክ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በዚህ ዓመት በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ867 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን እስካሁን በአጠቃላይ ከ17.6 ቢሊዮን ብር መገኘቱን የሚዲያ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...