Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዳግም የተከሰተው የጊኒ ዎርም በሽታ

ዳግም የተከሰተው የጊኒ ዎርም በሽታ

ቀን:

በሐሩራማ የትሮፒካል አካባቢ በ1970 ዓ.ም. የታየው የጊኒ ዎርም በሽታ ወረርሽኝ ተብለው ከተቀመጡ 20 ቀዳሚ በሽታዎች መካከል አንዱ ሆኖ በዓለም ጤና ድርጅት የተመዘገበ ነው፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ የተገኘባትም በጊኒ ሲሆን፣ ጊኒ ዎርም ከኩፍኝ ቀጥሎ ያለ መድኃኒት የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር ብቻ ሥርጭቱን መከላከል የሚቻል በሽታ መሆኑም ይወሳል፡፡

የጊኒዎርም በሽታ (Dracunculiasis/ድራኩንኩልያሲስ) ርዝማኔው ከ100 ሴንቲ ሜትር በላይ በሆነ ገመድ መሠል ትል የሚከሰትና አቅም የሚያሳጣ ነው፡፡

በአንድ የጤና ሚኒስቴር ሰነድ ላይ እንደተመለከተው፣ የንጹሕ መጠጥ ውኃ አለመኖር ዋነኛ መንስዔው ሲሆን፣ ትሉ ክፍት በሆኑ ኩሬዎች ውስጥ እንቁላሉን የሚጥል በመሆኑ ከዚያ ኩሬ ውኃ የጠጣ ሰው እንቁላሉን አብሮ ስለሚውጠው ትሉ ወደ ሰውነቱ ይገባል፡፡ በሰውነቱ ውስጥም ለአንድ ዓመት ያህል ምንም ሕመም ሳያሳይ ይቆያል፡፡ ከወገብ በታች በማሳከክና በማቁሰል ረዥም ትል ይወጣል፡፡ በዚህ ወቅት ታማሚው በአፋጣኝ ሕክምና ካላገኘ ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡

በተለያዩ አገሮች ጊኒ ዎርምን የማጥፋት ፕሮግራም አከናውነዋል፡፡  በኢትዮጵያም እየተከናወነ ሲሆን በተለይ ከዓመታት በፊት ትሉን የማጥፋት ተግባሩ የተሳካ መስሎ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ዓመት ወዲህ በተለይ በጋምቤላ ዳግም ማገርሸቱ ተገልጿል፡፡ 

አገራዊ የጊኒ ዎርምን ከኢትዮጵያ የማጥፋት ፕሮግራም ዓመታዊ ግምገማ ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲካሄድ በተገኙት የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ታንክዌይ ጆክ አገላለጽ፣ በክልሉ በቂ ንጹህ የመጠጥ ውኃ አለመኖር፣ ከፍተኛ የሰዎች ዝውውር መኖሩና የተቆፈሩ የውኃ ጉድጓዶችን በአግባቡ አለመጠቀም የጊኒ ዎርም በሽታ እንደገና እንዲከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ሆነዋል፡፡

የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው፣ የጊኒ ዎርም በሽታ ከኢትዮጵያ ለማጥፋት እንደ በሽታው ክስተት ዓይነትና መጠን በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በደረጃ የተለዩ ሲሆን፣ በአንደኛ ደረጃ የተቀመጠው ጋምቤላ ነው፡፡ በክልሉ የበሽታው ክስተት የተመዘገበባቸው አሁንም አዲስ ክስተት ያለባቸው ሁለት ወረዳዎች (ጎግ እና አቦቦ)፤ ደረጃ ሁለት የቅርብ ተጋላጭ የሆኑ 14 ወረዳዎች ማለትም ከጋምቤላ (11)፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ(1)፣ ከደቡብ ክልል(1) እና ከኦሮሚያ(1) ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ወረዳዎች በሽታው ካለባቸው አካባቢዎች ጋር ቅርበት የሌላቸው ናቸው፡፡

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እንዳሉትም፣ በሽታው በኢንስቲትዩቱ ከተለዩ 36 ሪፖርት የሚደረጉ በሽታዎች አንዱ ሲሆን፣ የሚያስከትለው ሞት አነስተኛ ቢሆንም በሕብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረው የሥነ ልቦና ተፅዕኖ ቀላል አይደለም፡፡

ንፅህናው ያልተጠበቀና በጥገኞች የተበከለን ውኃ በመጠጣት የሚከሰተው የጊኒ ዎርም በሽታ፣ በወረርሽኝ መልክ ተከስቶ የተለያዩ የዓለም አገሮችን በአንድ ወቅት አዳርሶ ነበር፡፡ በጊኒ ዎርም የተበከለን ውኃ በሚጠጣበት ጊዜ ዕጩ ወደ ሰው አካል ይገባል፡፡ ዕጩ በሰውነት ክፍል ውስጥ ወደ ትልነት የሚያድግ ሲሆን፣ እስከ አንድ ሜትር ይረዝማል፡፡

የጊኒ ዎርም በሽታ አስከፊነት ሰዎች በበሽታው መጠቃታቸውን የሚያውቁት በሰውነታቸው ውስጥ ለአንድ ዓመት ያህል ተሸሽጎ ከቆየ በኋላ ነው፡፡ 90 በመቶ የሚሆነው ከባድ የስቃይ ስሜት የሚሰማው በታችኛው የእግር ክፍል ነው፡፡

የጊኒ ዎርም በሽታ ትኩረት ከሚሹ ሐሩራማ በሽታዎች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሽታውን ለማጥፋት በተደረገው እንቅስቃሴ በብዙ አገሮች ማጥፋት እንደተቻለ የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ደረጀ ዱጉማ (ዶ/ር)፣ ሆኖም ኢትዮጵያን ጨምሮ በአምስት አገሮች በሽታው እንደሚገኝና ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ባለፉት ሦስት አሠርታት  ውጤታማ ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል፡፡

በተደረጉ የዘመቻ ሥራዎች በሽታውን ከ187 አገሮች ማጥፋት እንደተቻለ ቻድ፣ ማሊ፣ ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ ግን ከበሽታው ነፃ እንዳልነበሩ የዓለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2016 ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

በእነዚህ አገሮች በተለይም በኢትዮጵያ በተሠሩ የዘመቻ ሥራዎች ከጊኒ ዎርም ነፃ ለመሆን ጫፍ ላይ ደርሳ ነበር፡፡ ዳግመኛ የተከሰተው የጊኒ ዎርም ወረርሽኝም እንግዳ ነገር አሳይቷል፡፡ ከዚህ ቀደም ወረርሽኙ ከሰዎች በስተቀር በእንስሳት ላይ ታይቶ የማይታወቅ ቢሆንም በውሻና ዝንጀሮዎች ላይ መታየቱ ይታወሳል፡፡

ጊኒዎርም በአብዛኛው ጊዜ የሚያጠቃው ማኅበራዊ አገልግሎቶች ባልተዳረሱባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ማኅበረሰቦችን እንደሆነ ይወሳል፡፡

ጊኒዎርም መታከምና መዳን የሚችል ቢሆንም፣ ሕሙማን በግልጽ ወጥተው ወደ ሕክምና መሄድን ባለመምረጣቸው የማኅበረሰቡን በሽታን የመደበቅ ልማድ ለመስበር ጤና ሚኒስቴር በአንድ ወቅት ‹‹በበሽታው የተያዘ ሰውን ለጠቆመኝ እሸልማለሁ›› ብሎ ማስታወቂያ እስከማስነገር መድረሱ አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...