የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሐመድ ለኢፕድ የተናገሩት፡፡ ኃላፊው አያይዘውም፣ በግልም ሆነ በመንግሥት ከፍተኛ ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርታቸው ካጠናቀቁ በኋላ ብቃቸውን የሚያረጋግጥ አገር አቀፍ ፈተና ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡ የመውጫ ፈተና መስጠት ያስፈለገበት ዋናው ምክንያትም ምሩቃን ገበያው የሚፈልገውን አቅምና ብቃት ያሟሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ፣ በዓለም አቀፍ ገበያው ላይም ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግም ነው ሲሉም አክለዋል፡፡