Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የዳግማዊ ምኒልክ አማካሪ ሚኒስትር ውሎ

ትኩስ ፅሁፎች

አልፍሬድ ኢልግ ኢትዮጵያ ውስጥ አስር ዓመት ለሚሆን ጊዜ በአማካሪ ሚኒስትርነት ሲሠራ፣ ዋና ዋና ጉዳዮች ከነበሩት የመጀመሪያው የሀገሪቱን ነፃነት ማስጠበቅ፤ በመቀጠል አዳዲሶቹን ግዛቶች ማሳደግና ማስተካከል፣ ሌላው ደግሞ ብሔራዊ ኢኮኖሚን ማስፋፋት ነበር። በ1899 በምዕራብ ከወለጋ አውራጃ ወርቅ፣ ብርና ሌሎችን ማዕድናት የማውጣት፤ በዚያ ላይ የቴሌግራፍ መስመሮችን፣ ውኃ መስመሮችና መንገዶችን እንዲዘረጋ፣ ለእዚህም ባሩድና ፈንጂዎችን እንዲጠቀም ከንጉሡ ዘንድ ፈቃድ ተሰጠው። የማዕድን ኩባንያው በነፃነት መንቀሳቀስ ቻለ። አለመግባባቶችን የሚፈታ አንድ ራሱን የቻለ፣ ይህንን ጉዳይ እንዲመለከት ሥልጣን የተሰጠው ክፍል ተቋቋመ።  ከሚገኘው ገቢ ስምንት በመቶ፣ የድርሻውን አምስት በመቶ ለለቀቀው ለንጉሡ በቀረጥ መልክ ገቢ የሚደረግ ነው። ይህ ኩባንያም ከስኬቶቹ ጎን ለጎን ብዙ ችግሮችን ኢልግ ላይ አምጥቷል።

ሌዮ ሼፍኖ፣ የኢልግ የረዥም ጊዜ የሥራ ጓደኛና የባቡር ኩባንያው ፕሬዚዳንት፣ ሩሲያዊውን ጀብደኛ ግራፍ ሌኦንቲፍን የኢልን ሃሳብ ሳይጠይቅ ንግዱ ውስጥ ሊያስገባው ፈለገ። ጉዳዩ ጭራሽ ወደ ክርክር አመራ፣ በእርግጥ ኢልግ አሸናፊ ሆነ ለክርክሩ የወጣው ወጪ ተጠያቂ ከሩሲያ የመጣው ሰው ሆነ። የቤልጅየም የማዕድን ኩባንያ አጥጋቢ በሆነ መንገድ የከበሩ ድንጋችን፣ በተጨማሪም የድንጋይ ከሰል አገኘ። እንጨት ለግንባታ ሥራና ለማገዶ እንጂ ለማሞቂያ ጥቅም ላይ በማይውልበትና የደን መራቆቱ በጣም በተስፋፋበት ሁኔታ ይህ ግኝት ለሀገሪቷ ፍፁም አስፈላጊ አይደለም ሊባል አይችልም።

 በ1901/02 የጣና ሐይቅን የውኃ ኃይል የመጠቀምና ዓባይን ለሱዳን የመስኖ ልማት ጥቅም ላይ የማዋል እቅድ ወጣ። ኢልግ ለእንግሊዙ አምባሳደር ሃሪንግተን ዐፄ ምኒልክ ለእዚህ ፕሮጀክት ፍላጎት ያለው መሆኑን ያሳወቀው በዚህ መንገድ ነበር። ‹‹ንጉሡ ምኒልክ ጥቁር ዓባይና ጣናን በተመለከተ ከእንግሊዝ ውጪ ለማንም ፈቃድ መስጠት አይፈልግም።›› ለእዚህም ሥራ ፈቃድ አገኘ። በድፍረት የተሞላው ይህ እቅድ ግን ወደ ተግባር አልተተረጎም።
      ኢልግ ወደ አውሮፓ ባደረገው ሁለተኛ ጉዞ በንጉሡ ፍላጎት መሰረት ቪየና ውስጥ አንድ የሳንቲም ማተሚያ ማሽን አዘዘ፡፡ የካቲት 10 ቀን 1893 በወጣ ትዕዛዝ መሰረት ከአሁን በኋላ የኢትዮጵያ ሣንቲሞች ፓሪስ ሳይሆን አዲስ አበባ እንደሚታተሙ ተገለፀ።

  • ኸሪበርት ኩንግ (ትርጉም በዮናስ ታረቀኝ) ‹‹አማካሪው አልፍሬድ ኢልግ በዐፄ ምኒልክ ቤተመንግሥት››
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች