Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ሀገር ገዳም ትግባ

ትኩስ ፅሁፎች

ያኔ. . . . . . . .

በፍቅር ደግነት በሃይማኖት ፍሬ

በሀርቤ ላሊበላ በእምዬ ነገሥታት በአክሱም ኑባሬ

በአልማዝ በተጌጠ

በአልባስጥሮስ ብልቃጥ ናርዶስ በታጠበ

በደግነት ጥንስስ የፍቅርን ዝመራ

’ለም አንቆርቁራ

ከእግዜርም ጋር ኖራ

ለእግዜሩም ዘምራ. . . . . . . . . . .

አሁን ¡¡

አልቦ ተዋህዶ ወአልቦ ተፋቅሮ

ለክፋት ዘምሮ

እንትፍ እንደሚባል እንደጠላ ገፈት

ተፍተን ለሰበርነው ’ገርነት ሕይወት

በጸሎት አልቅሺ ብክዪ ኢትዮጵያ

ወንዝ ሙሉ እንባ

አትከላከሏት ትርጨው ወደ ሰማይ

እሪ ትበል ዋይ ዋይ

ከገዳሙ ትግባ

ከእግዜሩ ጋር ታውራ እልቅና ቢሾማት

ገዳም ቢያረጋት የሰማይ ሊጋባ

ሀገር ገዳም ትግባ።

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች