Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየመንግሥት ተሿሚዎች ሥልጣን ላይ ረግቶ አለመቆየትና መቀያየር በፓርላማ አባላት ጥያቄ አስነሳ

የመንግሥት ተሿሚዎች ሥልጣን ላይ ረግቶ አለመቆየትና መቀያየር በፓርላማ አባላት ጥያቄ አስነሳ

ቀን:

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የተሾሙ ሚኒስትሮች ሹመት በፓርላማ እንዲፀድቅ ሲቀርብ፣ የፓርላማ አባላት የመንግሥት ተሿሚዎች በሥልጣናቸው ረግተው እንዲቆዩ ማድረግ ለምን አልተቻለም ሲሉ ጥያቄ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥን ጨምሮ ለአራት ሚኒስትሮች ሹመት የሰጡት ከአንድ ሳምንት በፊት እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህም መሠረት ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር፣ ሀብታሙ ተገኝ (ኢንጂነር) የማዕድን ሚኒስትር፣ እንዲሁም ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የግብርና ሚኒስትር እንዲሆኑ በመሾም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያፀድቀው ልከው ነበር፡፡

ፓርላማው ማክሰኞ ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ዘጠነኛ መደበኛ ስብሰባ ከተገኙት የምክር ቤት አባላት መካከል አሥር አባላት ተቃውመው በሁለት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ የተሿሚዎቹ ሹመት ፀድቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ወ/ሮ አለ በላቸው የተባሉ የምክር ቤት አባል ሹመቱ ሴቶችን ያገለለ መሆኑን በመግለጽ፣ ‹‹የዛሬ ዓመት ነበር አስፈጻሚዎችን የሾምነው፣ ዛሬ ደግሞ በዓመቱ አዲስ ለመሾም የበቃነው ለምንድነው?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የአማራ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ አቶ ክርስቲያን ታደለ በበኩላቸው፣ ‹‹በ2014 ዓ.ም. የአስፈጻሚ አካላትን አዋቅረን ነው ሚኒስትሮችን የሾምነው፡፡ አገራችን የተረጋጋ አመራር፣ ሥርዓትና ቀጣይነት ያለው የተቋም ግንባታ ያስፈልጋታል የሚለው ዕሳቤ በሁሉም አካላት ስምምነት ተፈጥሮበት ያደረ ነጥብ ነው፡፡ ለምንድነው በየዓመቱ እንደ ዘመን መለወጫ ሚኒስትር የምንቀያይረው? ለምንድነው በአንፃራዊነት ተቋም መገንባት የሚችሉ አመራሮችን አጥንተንና በደንብ መርምረን ማምጣት ያልቻልነው? በየጊዜው የሚካሄደው የአመራር ለውጥ መቀያየርስ ማብቂያው መቼ ነው?›› ብለዋል፡፡

አቶ ክርስቲያን አክለውም ተሿሚዎቹ የሚመሯቸውን መሥሪያ ቤቶች የሚከታተሏቸው ቋሚ ኮሚቴዎች ስለግለሰቦቹ ማንነት እንዲያጠኑና እንዲገመግሙ ቢደረግ፣ ከተቋማት ባህሪ አንፃር ምን ዓይነት አመራር ሊሰጡ ይችላሉ የሚውን ለመለየትና ቀጣይነት ያለው ተቋም ለመገንባት የሚያግዝ የተሻለ ሥራ መሥራት ይቻል እንደነበር አስረድተዋል፡፡

የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትሩ አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ ለተነሱት ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ፣ የተሰጡት ሹመቶች ግለሰቦቹ ከዚህ ቀደም በተሰማሩበት ቦታ በውጤታማት፣ በቅንነትና በታማኝነት አገርን ያገለገሉ በመሆናቸው ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይ አንገብጋቢ የሆኑ የሕዝብ ጥያቄዎችን በፍትሐዊነት ከመመለስ አንፃር ታሳቢ ተደርጎ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የሴቶች ተሳትፎን በተመለከተ መንግሥት በአጠቃላይ አመራርን ሲያደራጅ የሴቶች፣ የወጣቶችና የምሁራን በሚል መልስ በሚሰጥ ሁኔታ እንደሚያከናውን፣ ነገር ግን አሁን እንደተካሄደው ሁሉ በየመሀሉ እንዲህ ዓይነት ለውጦች ሲደረጉና ወደ ሥራ ከተገባ በኋላ መንግሥት ሥራውን እየገመገመ አመራርን የማሸጋሸግና የመደልደል ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን ያለው በመሆኑ፣ ከአሠራር አኳያ ችግር እንደሌለው አስረድተዋል፡፡

የአመራር ምደባን በተመለከተ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 74 መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕጩ ማቅረባቸውን የገለጹት አቶ ተስፋዬ፣ የሚኒስትሮች ሹመት አቀራረብም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕገ መንግሥቱ በተሰጣቸው ሥልጣን መሠረት እንደሆነና አሁን ያለው የተሿሚ አቀረራብ አሠራር በቋሚ ኮሚቴ በኩል ይለፍ የሚል አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...