Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትብሔራዊ ቡድኑ በታቀደለት ቀን ወደ አገር ቤት ባለመመለሱ ሊጉ ለሳምንት ተራዘመ

ብሔራዊ ቡድኑ በታቀደለት ቀን ወደ አገር ቤት ባለመመለሱ ሊጉ ለሳምንት ተራዘመ

ቀን:

በአልጄሪያ ቨሰባተኛው የአፍሪካ አገሮች ሻምፒዮና (ቻን) ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በታቀደለት ቀን ወደ አገር ቤት መመለስ ባለመቻሉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር መርሐ ግብሩን ለአንድ ሳምንት ማስረዘሙን አስታውቋል፡፡

ዋሊያዎቹ ከአልጄሪያ ወደ አዲስ አበባ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ የበረራ ትኬቱ ባለመገኘቱ መስተጓጎሉ ተገልጿል፡፡

በምድብ አንድ ከአዘጋጅዋ አልጄሪያ፣ ሊቢያና ሞዛምቢክ ጋር የተደለደለው ብሔራዊ ቡድኑ ካደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ ከውድድሩ በጠዋቱ መሰናበቱን ተከትሎ በቻን የተሰጠውን ያህል ቆይታ ባለማድረጉ የመመለሻ ቀኑ ላይ ለውጥ ሊደረግ ችሏል፡፡

በዚህም መሠረት በውድድሩ ቆይታ ሊኖረው ይችላል በሚል የደርሶ መልስ ትኬት ተቆርጦለት የነበረው ብሔራዊ ቡድኑ እንደታሰበው በውድድሩ ባለመቆየቱ የመመለሻውን ቀን መለወጥ በመገደዱና በሰዓቱም የበረራ ትኬት በመጥፋቱ ሊዘገይ እንደቻለ ተነግሯል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ሰኞ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. የሊጉ መርሐ ግብር ከቆመበት የሚቀጥልበትን የጨዋታ ቀን ይፋ ቢያደርግም በማግሥቱ ለአንድ ሳምንት ማስረዘሙን ይፋ አድርጓል፡፡

በአዳማ ከተማ የሚካሄደው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥር 20 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደሚጀመር ለክለቦች መገለጹን የጠቀሰው አክሲዮን ማኅበሩ፣ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ማኅበር አገኘሁት ባለው መረጃ መሠረት ለአንድ ሳምንት ማራዘሙን ገልጿል፡፡

ቀድሞ በወጣው መርሐ ግብር መሠረት ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች የ12ኛ ሳምንቱ የቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ቅዳሜ ጥር 20 ቀን እንዲሁም የ11ኛ ሳምንት የወላይታ ድቻና የሲዳማ ቡና እሑድ ጥር 21 ቀን እንደሚካሄዱ መርሐ ግብር ተይዞላቸው ነበር፡፡

በተጨማሪም ከ14ኛ እስከ 19ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች ከጥር 25 እስከ መጋቢት 3 ቀን ድረስ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንደሚካሄድ መገለጹ ይታወሳል፡፡

በአንፃሩ መርሐ ግብሩ በአንድ ሳምንት መራዘሙን ተከትሎ ጨዋታዎቹ ጥር 27 ቀን እንደሚጀምሩ አክሲዮን ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

በቻን ደካማ እንቅስቃሴ ያደረገው የዋሊያዎቹ ስብስብ ይኼ ዘገባ እስከ ተጠናቀረበት ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለስበት ቀን አልታወቀም፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀጥታ ወደ አልጄሪያ በረራ ስለሌለው የሌላ አገር አየር መንገድ ለመጠቀም መገደዱ የተገለጸ ሲሆን፣ ግብፅ ላይ ለሰዓታት አርፎ ወደ አዲስ አበባ በረራ ለማድረግ አማራጭ ለማድረግ ማቀዱም ተሰምቷል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ሌላ አማራጭ ወይም የቻርተር አውሮፕላን ለመጠቀም የገንዘብ አቅሙ እንዳልፈቀደለትም ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...