Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሕንፃ በደረሰበት ቃጠሎ የ60 ሚሊዮን ብር ጉዳት መድረሱ...

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሕንፃ በደረሰበት ቃጠሎ የ60 ሚሊዮን ብር ጉዳት መድረሱ ተገለጸ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አደጋ 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን፣ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በክፍለ ከተማው አስተዳደር ሕንፃ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት እንደወደመ፣ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

የእሳት አደጋው የተከሰተው ሰኞ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ከምሽቱ 4፡58 ሰዓት ሲሆን፣ በአደጋው ሦስት የኮሚሽኑ ሠራተኞችን ጨምሮ አሥር ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አቶ ንጋቱ ለሪፖርተር የላኩት መረጃ ይገልጻል፡፡  

በእሳት ወደመ የተባለው ሕንፃ ባለሰባት ወለል ሲሆን፣ አደጋውን ለመከላከልም 65 የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችና አሥር ተሽከርካሪዎች ተሰማርተው እንደነበር አቶ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ፣ አደጋውን ያደረሱት አካላት ማንነት ለጊዜው ማወቅ እንዳልተቻለና ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የክፍለ ከተማው የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት አስናቀ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ክፍለ ከተማው ሕንፃውን የተከራየው ከግል ባለሀብት ላይ ነው፡፡  

ሕንፃው ቅዳሜ ጥር 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ተመርቆ ሙሉ ሥራ ለመጀመር ታቅዶ እንደነበርም ወ/ሮ ወይንሸት አስረድተዋል፡፡

የቃጠሎ አደጋ ደረሰበት የተባለው ባለሰባት ወለል ሕንፃ ንብረትነቱ የግለሰብ ቢሆንም፣ የከተማ አስተዳደሩ ሥራ ለመጀመር ወጪ አውጥቶበት እንደበርና ውድመት እንደገጠመውም አውስተዋል፡፡

አክለውም፣ የከተማ አስተዳደሩ ያወጣው ወጪና የወደመው የንብረት ግምት እየተሠላ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ክፍለ ከተማው ሕንፃውን አስመርቆ ወደ ሥራ ለመግባት በነበረው ዝግጅት ኢትዮ ቴሌኮም፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ተቋማት የዳታ ማዕከሉን ዲጂታል በማድረግ ተሳትፈዋል ተብሏል፡፡

የእሳት አደጋው ከምድር ቤቱ ጀምሮ እስከ ሁለተኛው ፎቅ ቢደርስም፣ ወደ ክፍለ ከተማው ሕንፃ የገባ መረጃ ስላልነበረ በሕዝብ ፋይል ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ተጠቅሷል፡፡

የክፍለ ከተማው አስተዳደር ሥራ ለመጀመር ሲያስብ ያሟላቸውና ወደ ቢሮ ያስገባቸው ዕቃዎች ውድመት የደረሰባቸው መሆኑን፣ ውጭ የነበሩ የቢሮ ጠረጴዛዎች ግን ጉዳት እንዳልደረሰባቸው የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡

የደረሰው አደጋ በእሳት መቀጣጠል ወይም ሆን ተብሎ በሰዎች የደረሰ መሆኑን ገና ማወቅ ባይቻልም ሲታወቅ ይፋ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል ሰኞ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ደረሰ ከተባለው የእሳት አደጋ በተጨማሪ፣ ሌሎች ሁለት አደጋዎች እንደተከሰቱ፣ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለሪፖርተር በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡

መረጃው እንደሚያሳየው ከሆነ ከላይ በተጠቀሰው ዕለት ከምሽቱ 3፡55 ሰዓት በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስኮ መናኸሪያ በሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል፡፡

በሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሱ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋም አንድ ሚለዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በሸገር ከተማ ቡራዩ በሾፌን ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ደርሷል በተባለ የእሳት አደጋ ከ300 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት ንብረት እንደወደመ፣ አደጋው የተከሰተውም ከቀኑ 10፡46 ሰዓት እንደነበር የኮሚሽኑ መረጃ ያሳያል፡፡

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ አክለውም፣ የለሚ ኩራውን አደጋ በተመለከተ ሰኞ ጠዋት ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. 1.6 ሚሊዮን የሚገመት ንብረት ወድሞ እንደነበር መግለጻቸውን አስታውሰው፣ ለሪፖርተር ግን 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል በሚል እንዲስተካከል ጠይቀዋል፡፡

በአጠቃላይ በአንድ ቀን ተከሰቱ የተባሉ የእሳት አደጋዎችን ለመቆጣጠር በተደረገ ጥረት፣ 250 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መታደግ ስለመቻሉ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...