Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ‹‹አንድ አባወራ ለአንድ እንግዳ››

‹‹አንድ አባወራ ለአንድ እንግዳ››

ቀን:

በወርኃ ሐምሌ 1994 ዓ.ም. ነው፡፡ ከካናዳ ከመጣችው አብሮ አደግ ጓደኛዋ ጋር ዘመድ ጥየቃ ወደ ጎንደር ያቀናሉ፡፡ ጎንደር አዘዞ፡፡ በአዘዞ ዛሬ ላይ ስሙን በቅጡ በማታስታውሰው አረንጓዴ ገጠራማ አካባቢ ያቀኑት የጓደኛዋን አያት ለመጠየቅ ነበር፡፡

ከአውሮፕላን ማረፊያ የተቀበላቸው ዘመድ ከአያትየው ቤት እንዳደረሳቸው የአካባቢው ሰው ‹የልጅ ልጃቸው መጥታለች› ተብሎ ወደተነገረላቸው ‹‹እታታ ቤት›› መምጣት ጀመረ፡፡ የአካባቢው ታዳጊዎች ሁሉ መጥተው እንደነበር ታስታውሳለች፡፡

ጎንደር አዘዞን ለመጀመርያ ጊዜ በረገጠችበት ዕለት የተመለከተችው የየጎረቤቱን አቀባበል ዛሬ ድረስ አትረሳውም፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከየጎረቤቱ መጥተዋል የተባሉትን እንግዶች ለማየት የመጡ ነዋሪዎች በሙሉ ባዶ እጃቸውን አልነበሩም፡፡ ለስላሳ፣ ዳቦ፣ እንጀራና ሌሎችን ይዘው ነበር፡፡ እቅፍ እያደረጉ እንደ ልጆቻቸው አገላብጠው እየሳሙ ለአያትየው ‹እንኳን ደስ አለሽ እታታ› እያሉ ደስታቸውን ይገልጹም ነበር፡፡ ‹‹ፊታቸው ላይ የነበረው የደስታ ስሜት ዛሬም ከ20 ዓመታት በኋላ አይረሳኝም ትላለች››፡፡

ከካናዳ ለመጣችውም ሆነ አብራት ከአዲስ አበባ ለሄደችው ጓደኛዋ እንግዳን መቀበል አዲስ ባይሆንም እዚያ የተመለከቱት ግን አስደምሟቸዋል፡፡ የየአካባቢው ሰው ሁሉ እየተጠራራ በእጅ የሚቀመስ ነገር ይዞ ቤቱን ሞልቶታል፡፡ ‹‹በወጣትነት አዕምሮ የተቀረጸ ደስ የሚል የእንግዳ አቀባበል ነበር›› ስትል ሁኔታውን ታስታውሰዋለች፡፡

ይህ በጎንደር ያየችውን የእንግዳ አቀባበል በሥራ አጋጣሚ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በትግራይና በሌሎች አካባቢዎችም ስትዘዋወር መታዘቧን ነግራናለች፡፡ ‹‹ከአዲስ አበባ በወጣሁባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ በተለይ በየገጠሩ ያለው አቀባበል ይገርመኛል፡፡ ያላቸውን እንድትቀምሽላቸው፣ ስብስብ ብለው በመቀመጥ እንድታወጊያቸው የሚፈልጉ ናቸው፤›› ትላለች፡፡

መንገድ ለጠፋው ‹‹እንግዳ ይሆናል ንገሩት/ንገሯት››፣ ማዕድ ሲቀርብ ‹‹መጀመርያ እንግዳ ይስተናገድ›› የሚሉት አባባሎችም ለብዙዎች እንግዳ አይደሉም፡፡

ጎንደርም የ2015 ዓ.ም. የከተራ፣ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓላትን አስመልክቶ ወደ ከተማዋ የገቡ እንግዶችን አስተናግዳለች፡፡ ጥምቀት በድምቀት ከሚከበርባቸውና የቱሪስት መዳረሻ ከሆኑ ሥፍራዎች ከቀዳሚዎቹ በምትጠቀሰው ጎንደር ነዋሪው ‹‹አንድ አባወራ ለአንድ እንግዳ›› በሚል የቀረበውን ጥሪ ተቀብሎ እንግዶችን አስተናግዷል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የመኝታ ቦታ ላልያዙና የመኝታ ጥበት የሚያጋጥማቸው ቢኖር ‹‹አንድ አባወራ አንድ እንግዳ›› እንዲያስተናግድ በጠየቀው መሠረት በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች አድራሻቸውን ለከተማ አስተዳደሩ በመስጠት የተቻላቸውን ያህል እንግዶች አስተናግደዋል፡፡

መሪጌታ ደሴ መኳንንት እንግዶችን ተቀብለው ካስተናገዱ በጎ ፈቃደኞች አንዱ ናቸው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ ትርፍ አልጋ ያላችሁ፣ በቤታችሁ ማስተናገድ የምትችሉ እንግዳ ተቀበሉ ሲባል የባህል ሕክምና በሚሠሩበት ቤት እንግዳ ማስተናገድ እንደሚችሉ አምነው በበጎ ፈቃደኝነት ስልካቸውን በመስጠት እንደ ቤተሰብ እንግዶችን አስተናግደዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ለጥምቀት እንግዳ በበጎ ፈቃድ አስተናግደው እንደማያውቁ፣ ዘንድሮ ግን አምስት ሰዎችን ማስተናገዳቸውን ነግረውናል፡፡

በጎንደር ቀዝቅዞ የቆየው ሥርዓት ዘንድሮ በተለየ በድምቀት መከበሩ፣ የሰዉም አቀባበልና የእንግዳው ሥነ ሥርዓት፣ እሳቸውም እንደ ቤተሰብ እንግዶችን አስተናግደው በመሸኘታቸው መደሰታቸውን አክለዋል፡፡

አቶ መስጠት አረጋ ሌላው እንግዳ ተቀብለው ካስተናገዱ የከተማዋ ነዋሪዎች ውስጥ ይገኙበታል፡፡ ‹‹እኛ በተቻለ መጠን አስተናግደናል›› የሚሉት አቶ መስጠት፣ ለስምንት እንግዶች አልጋ ይዘው፣ ሦስት ደግሞ በቤታቸው ከቤተሰብ ጋር ማስተናገዳቸውን ገልጸዋል፡፡

የሞባይል ሴንተርና ካፌ ባለቤት የሆኑት አቶ መስጠት፣ ለከተማ አስተዳደሩ ስልክ ሰጥተው መገኛቸው አድራሻቸው በአስተዳደሩ ማኅበራዊ ገጽ ከተለቀቀ በኋላ የደወሉላቸውን ሰዎች ከመኝታ ባለፈ ምግብም ችለው እንደሸኟቸው ነግረውናል፡፡

‹‹እንግዳ በመተዋወቄ እነሱ ሳይሆኑ እኔ ተጠቅሜያለሁ፣ በዓልን ለማክበር ቢመጡም እንኳ ስጦታ ሰጥቼ ሸኝቻለሁ፡፡ ከማስተናገድ ባለፈ ጓደኝነት፣ ቤተሰብነት ተሰምቶኛል፣ አድራሻ ተለዋውጠናል፤›› ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...