-የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ከአኃላፊነታቸው ተነሱ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ(ዶ/ር) በቅርቡ ከኃላፊነታቸው በተነሱት የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ(ኢንጂነር) ምትክ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ተገኝ(ኢንጂነር)ን፣ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሯ በወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ምትክ ደግሞ አለሙ ስሜ(ዶ/ር)ንና በግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሁሴን ምትክ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)ን መሾማቸውን ጽሕፈት ቤታቸው አስታወቀ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌሎችንም ሹመቶችን የሰጡ ሲሆን፣ ከጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ማሞ ምሕረቱ – የብሔራዊ ባንክ ገዢ፣ ወይዘሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር፣
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር፣ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር እና አቶ መለሰ አለሙ – በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ የዘርፍ አስተባባሪ ሆነው ተሹመዋል፡፡