Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአዲስ አበባ ሁለተኛው ታላቅ አደባባይ በ1.3 ቢሊዮን ብር ሊገነባ ነው

በአዲስ አበባ ሁለተኛው ታላቅ አደባባይ በ1.3 ቢሊዮን ብር ሊገነባ ነው

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ውስጥ በ1.3 ቢሊዮን ብር በጀት፣ አዲስ የሕዝብ አደባባይ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ በማስቀመጥ ሥራው ተጀመረ፡፡

ሥራውን በይፋ ጥር 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሲሆኑ፣ የአደባባዩ መጠርያም ‹‹ለሚ አደባባይ›› ነው፡፡

ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ሁለተኛው የሚሆነው የለሚ አደባባይ ፕሮጀክቱ 14,400 ካሬሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን የሕዝብ ስፍራ አደባባይ (ፐብሊክ ስፔስ)፣ የመኪና ማቆምያ፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ጂምናዝዬሞችን፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ፣ የሠርግና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውል መናፈሻ፣ ሱፐርማርኬት፣ የቢሮ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎች፣ መጻሕፍት የማንበቢያ ስፍራና የመሳሰሉት ይኖሩታል፡፡

አካባቢውንም በማስዋብ ከመንገድ አካፋዮች፤ አደባባዮችንና የእግረኛ መንገዶች ጋር ተናቦ የሚሠራ ሁለንተናዊ ፕሮጀክትም ነው ተብሎለታል፡፡

የከንቲባ ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው፣ ይህ ፕሮጀክት በግንባታው ወቅት እስከ ለ1100 ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ሲሆን፣ በቀጣይ በቋሚነት ለ400 ሰዎች የሥራ ቦታቸው የሚሆን ነው፡፡

ሥራው ሌትና ቀን ያለ ዕረፍት በመሥራት በ10 ወራት ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅ የገለጹት ከንቲባ አዳነች፣ በጋራ ኃላፊነት አብሮ በመሥራትና በመተባበር የታሰበው ፕሮጀክት ዕውን ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቶች በመሃል ከተማ ብቻ ሳይሆኑ በዳር አካባቢዎችም ማዳረስን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ የተነገረለት የለሚ አደባባይ ፕሮጀክት፣ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት ከጥበብ ዲዛይንና ቢዪልዲንግ ፒኤልሲ ጋር በመተባበር ተገንብቶ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ቦታው የተመረጠበት ዋነኛ ምክንያት አዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በአካባቢው እየተገነባ ያለ በመሆኑ ነው ያሉት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች፣ አካባቢው ተጨማሪ አገልግሎቶችና ተያይዘው የሚመጡ ስፍራዎች የሚያስፈልጉት መሆኑንም አውስተዋል፡፡

ከተማዪቱን ከዘመኑ ጋር የዘመነ አሠራርና አስተሳሰብ በመያዝ ነው መቀየር የሚቻለው ያሉት ከንቲባዋ፣ የግሉን ሴክተር በማሳተፍ የመንግሥትን ክፍተት በመሙላትና በአጭር ጊዜ ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ ዕውን ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...