ብፁዕ አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የ2015 ዓ.ም. የጥምቀት በዓል አከባበርን አስመልክቶ የተናገሩት። ፖለቲከኞች የቤተ ክርስቲያኒቱን በዓል እንደ ቤተክርስቲያን አክብሩ ያሉት ሊቀ ጳጳሱ፣ ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጡ የፖለቲካ ካባችሁን አውልቃችሁ፣ የቤተ ክርስቲያንን ካባ ለብሳችሁ ፍቅርና ትህትናን በተላበሰ መልኩ በዓሉን አክብሩ ብለዋል። ማንም ሰው ወደዚህ ሲመጣ የቤተ ክርስቲያንን ክብር መጠበቅ ይኖርበታል በማለትም አጽንዖት ሰጥተውበታል።