Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየክብር ዶክትሬቷን የተቀበለችው በኩር ድምፃዊት ማሪቱ ለገሠ

የክብር ዶክትሬቷን የተቀበለችው በኩር ድምፃዊት ማሪቱ ለገሠ

ቀን:

ከአምስት አሠርታት በላይ ባስቆጠረው የሙዚቃ ሕይወቷ፣ በባህል ድምፃዊነት ገናና የሆነችው በኩር ድምፃዊት ማሪቱ ለገሠ፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬትን ጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በደሴ ካምፓሱ ባዘጋጀው ሥነ ሥርዓት ሰጥቷታል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ክብሩን ድምፃዊቷ በሌለችበት ከሰባት ዓመት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በአራቱ የሙዚቃ ቅኝቶች በአምባሰል፣ ባቲ፣ አንቺ ሆዬና ትዝታ እያለዋወጠች በመዝፈን በባህላዊው ሙዚቃ ልዕልናን ያገኘችው ማሪቱ፣ በተለይ ‹‹የአምባሰል ንግሥት›› እየተባለችም ትጠራለች፡፡ ከመስከረም እስከ መስከረም የባህል ልብስ በመልበስ የምትታወቀው ማሪቱ፣ በኢትዮጵያ በሚኖራት የሦስት ወራት ቆይታዋ አዲሱን አልበሟን ለኅብረተሰቡ የምታደርስ ሲሆን፣ የሙዚቃ ሥራዎቿን በደሴ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳርና አዲስ አበባ እንደምታቀርብ ታውቋል፡፡ ማሪቱ ከ1971 ዓ.ም. ጀምሮ በአብዮታዊ ኢትዮጵያ ገንኖ የነበረው በተለይ ‹‹ፈጣን ነው ባቡሩ›› በሚለው ኅብረ ዝማሬው በሚታወቀው የወሎ ላሊበላ የኪነት ቡድን ውስጥ መሪ ድምፃዊት ነበረች፡፡ ከሁለት አሠርታት በላይ በአሜሪካ ኑሮዋን አድርጋ የነበረችው ድምፃዊቷ፣ ታኅሣሥ 24 ቀን ወደ ኢትዮጵያ መመለሷ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...