Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሴቶች ብቻ ዕውቅና የሚያገኙበት የ‹‹ድንቅነሽ ሽልማት›› ሊሰጥ ነው

ሴቶች ብቻ ዕውቅና የሚያገኙበት የ‹‹ድንቅነሽ ሽልማት›› ሊሰጥ ነው

ቀን:

በየዓመቱ ‹‹ማርች 8›› (የካቲት 29 ቀን) የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ የዓመቱ ምርጥ ሴቶች ዕውቅናና ምስጋና የሚያገኙበት ‹‹ድንቅነሽ ሽልማት›› የተሰኘ ሽልማት ሊሰጥ ነው፡፡

የመጀመርያ የዕውቅና ሽልማቱን የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚሰጥ መሆኑን አስመልክቶ አርኪ ፕሮሞሽንና ኢቨንት ጥር 4 ቀን እንዳስታወቀው፣ ሽልማቱ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ለአገራቸውና ለማኅበረሰባቸው የላቀና የተለየ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ጠንካራና ብርቱ ሴቶች የሚሰጥ ይሆናል፡፡

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሸምሱ ከሪም እንዳሉት፣ ‹‹ድንቅነሽ ሽልማት›› በመምህርትነት፣ በስፖርት፣ በጋዜጠኝነት፣ በሕክምና፣ በውትድርና፣ በኪነ ጥበብ፣ በፈጠራ፣ በበጎ አድራጎት፣ በአመራርና በአምባሳደርነት ዘርፎች የሚሰጥ ነው፡፡

በአሥር ዘርፎች የሚወዳደሩ ዕጩዎችን ጥቆማ ከማኅበራት፣ ከተቋማትና ከሌሎችም እያሰባሰቡ ሲሆን፣ ማኅበረሰቡ ጥቆማ የሚሰጥበት የቴሌግራም ቻናል መከፈቱንም ተናግረዋል፡፡

በማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዕለት ለመስጠት የታሰበው ‹‹ድንቅነሽ ሽልማት›› የዘንድሮው የመጀመርያ በመሆኑ ማኅበረሰቡ ከመጠቆም ባለፈ ድምፅ የሚሰጥበት አሠራር እንደሌለ የገለጹት የድርጅቱ ፕሮዳክሽን ማናጀር ስህነማርያም አበበ፣ ውጤቱ በሕዝብ ዘንድ ተዓማኒነት ባተረፉ ዳኞች ተወስኖ በቦርድ አባላት የሚፀድቅ ይሆናል ብለዋል፡፡

እስካሁን ባለው ሒደት ከአዲስ አበባ ውጭ ከክልሎችም ዕጩዎች እየተጠቆሙ መሆኑን፣ በቀጣይም ዕጩዎች ከመላ ኢትዮጵያ እንዲጠቆሙ እንደሚሠራም ገልጸዋል፡፡

በሕይወት የሌሉና በልዩ ሁኔታ የሚሸለሙ ሴቶች በመጀመርያው ዙር እንደማይካተቱም አክለዋል፡፡

ሽልማቱ አንድ ጊዜ ተጀምሮ እንዳይቋረጥ እንደሚሠራ፣ ለዚህም ከተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ጋር አብሮ ለመሥራት እንቅስቃሴ መጀመሩን አቶ ሸምሱ ተናግረዋል፡፡

‹‹ድንቅነሽ ሽልማት›› ከሚመለከተው አካል እውቅና ማግኘቱን፣ ጥቆማዎች ከማኅበረሰቡና ከተቋማት ከመጡ በኋላ ጥናት ተካሂዶ ተሸላሚዎች እንደሚለዩም ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...